“ብርሃን ዘኢትዮጵያ” የእቴጌ ጣይቱ 182ኛ ዓመት ልደት በደብረ ብርሃን ከተማ ተከበረ፡፡

155

ደብረ ብርሃን: ነሐሴ 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ለመላው ጥቁር ሕዝብ የነጻነት ምልክት የኾነው የዓድዋ ድል እንዲገኝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራቸው እና ለኢትዮጵያ ትንሣኤ ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉት እቴጌ ጣይቱ (ብርሃን ዘኢትዮጵያ) ልደት በደብረ ብርሃን ከተማ ተከብሯል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ገነት ቤተ እቴጌ ጣይቱ የመሪነት ጥበብ በሚገባ የታደሉ፣ ብቁ ዲፕሎማት እና ለዘመናዊት ኢትዮጵያ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራቸው ሰው እንደነበሩ አስረድተዋል፡፡ የዚህ ትውልድ ሴት አመራሮችም የዘመኑ እቴጌ ጣይቱ ብጡል መኾን ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ወይዘሮ የለም ሸዋ በቀለ ‟ታሪኮቻችንን በሚገባ በመዘከር ታሪኩን የሚያውቅ ትውልድ መፍጠር እና ከቱሪዝሙ ዘርፍ የሚገኘውን ገቢ ማሳደግ ተገቢ ነው” ብለዋል፡፡

የከተማው የሥራ ኀላፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የልደት በዓል በድምቀት ተከብሯል፡፡

ዘጋቢ፡- ገንዘብ ታደሰ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼

ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼

Previous articleአሽንድዬ፣ የወርቃማዋ ምድር ጌጥ- የላስታ ትሩፋት!
Next articleወደ ተኩስ አቁም ስምምነት ሊያደርስ የሚችል እና ለቀጣይ የፖለቲካ ውይይቶች መሠረት የሚጥል የሰላም ምክረ ሐሳብ ሰነድ ጸደቀ።