“በቃላችን መሠረት፣ ማንም ላይ ጉዳት ሳናደርስ እነሆ 3ኛውን ዙር ውኃ ሙሌት በታሰበው ጊዜ ማጠናቀቅ ስለቻልን የዓባይ ልጆች ሁሉ እንኳን ደስ ያለን!!” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

98

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሕዳሴ ግድብ 3ኛው ዙር ውኃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቅን በማስመልከት በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ በቃላችን መሠረት፣ ማንም ላይ ጉዳት ሳናደርስ 3ኛውን ዙር ውኃ ሙሌት በታሰበው ጊዜ ማጠናቀቅ ችለናል ብለዋል።

“ዓባይ ላይ ግድብ ለመገንባት ስንነሳ ወንዙን የራሳችን ብቻ የማድረግ ፍላጎት አድሮብን እንዳልሆነ ከመጀመሪያውም ስንናገር ነበር፡፡ እኛ ማግኘት የሚገባንን ጥቅም እናግኝ ስንል ልክ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ ሌሎቹ የዓባይ ሥጦታዎች – ሱዳንና ግብጽ ከወንዙ በየድርሻቸው እንደሚጠቀሙበት እያሰብን ጭምር ነው፡፡ እውነትን ይዘን ተነስተን፣ በገዛ ሐቃችን ገንብተን፣ በቃላችን መሠረት፣ ማንም ላይ ጉዳት ሳናደርስ እነሆ 3ኛውን ዙር ውኃ ሙሌት በታሰበው ጊዜ ማጠናቀቅ ስለቻልን የዓባይ ልጆች ሁሉ እንኳን ደስ ያለን!!” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

የዓባይ ወንዝ ለሺህ ዘመናት ሦስቱን ሀገራት አስተሳስሮ እንዳኖራቸው ሁሉ፤ በእሱ ላይ የተገነባው ግድብ ከሌሎች ጎረቤቶቻችንም ጋር በትብብር እንድንኖር ያስችለናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ግድቡ ደለል የሚያስቀር በመኾኑ በጎርፍ ምክንያት በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የሚወድመውን ሀብትና የሚጠፋውን የሰው ሕይወት ቁጥር እንደሚቀንስ ይታወቃል ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ ግድቡ የሚያመነጨውን ኤሌክትሪክ – በኃይል ምንጭነት፣ በውኃው አናት ላይ የሚነጠፈውን ውብ ገጽታ -በመዝናኛነት፣ በውኃው ጉያ የሚሰግሩትን አሳዎች – በምግብነት ከጎረቤቶቻችንና ከዓለም ጋር እንጋራዋለን ብለዋል በመልእክታቸው፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼

ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article❝የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በማንኛውም ሰው ሠራሽ ጫናዎች ሳይበገር ለዚህ ታላቅ ውጤት መብቃቱ የትውልዱ ፅናት እና ትብብር ማሳያ ነው❞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
Next article❝ኢትዮጵያ ልጇን አዘዘችው፣ በቤቷም አሳደረችው❞