
ነሐሴ 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ባስተላለፉት መልዕክት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት መርኃግብር በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን አብሮ ደስ አለን ብለዋል።
ለዘመናት ቁጭት እያወረሰ ይፈስ የነበረው የዓባይ ወንዝ ደረጃ በደረጃ የተግባር መላሹን እያጠበቀ ለሁለተኛ ጊዜ ኃይል በማመንጨት ታላቅ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ደርሷል ነው ያሉት።
የአንድነታችን መገለጫ “የሕብረታችን ማረጋገጫ የኾነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በሂደት ወደ ማጠናቀቂያ ምዕራፍ መሸጋገሩን ቀጥሏል” ብለዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በማንኛውም ሰው ሠራሽ ጫናዎች ሳይበገር ለዚህ ታላቅ ውጤት መብቃቱ የትውልዱ ፅናት እና ትብብር ማሳያ ነው ያሉት አቶ ደመቀ
ባለፉት ዓመታት እንደሀገር ከገጠሙን የሰላምና የፀጥታ ችግሮች አኳያ የግድቡ ግንባታ ሳይስተጓጎል በተቀመጠለት የጊዜ ማዕቀፍ ማስቀጠል መቻላችን ፈተና ይበልጥ ያፀናን እንደኾን እንጂ ከቶውኑ እንደማይጥለን በተግባር ያረጋገጥንበት ነው ብለዋል።
ለግድቡ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት አባላት፣ የፕሮጀክቱ አመራሮች እና ባለሙያዎች፣ የፀጥታ አካላት፣ ባለሃብቶች፣ ዳያስፖራ ማኅበረሰብ እና መላው ኢትዮጵያውያን ለግድቡ ስኬት ላበረከተቱት አስተዋጽኦ ምሥጋና አቅርበዋል።
በቀሪ የግድቡ ማጠናቀቂያ ምዕራፍ ሥራዎች ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድነቱን ይበልጥ እንዲያጠናክርና እና ሕብረቱን እንዲያፀናም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
