❝የኢትዮጵያ አየር ኃይል የአየር ክልሉን ከማንኛውም ጥቃት መጠበቅና መከላከል የሚያስችል ቁመና ላይ ነው❞ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ

321

ነሐሴ 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሀገሪቷን አየር ክልል ከማንኛውም ጥቃት መጠበቅና መከላከል የሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ የአየር ኃይሉ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከ93 ዓመት በፊት በአፍሪካ የመጀመሪያ አየር ኃይል ኾኖ የተመሠረተ አንጋፋ ተቋም ነው።

በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ነሐሴ 12/1921 ዓ.ም ‘ጃን ሜዳ’ ላይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምሥረታ ከተበሰረ በኋላ በ1954 ዓ.ም በኮንጎ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ የጎላ ተሳትፎ ማድረጉም ተመልክቷል፡፡

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ ለኢዜአ እንዳሉት፤ አየር ኃይሉ ቴክኖሎጂ በማፍለቅና የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት በ2022 ዓ.ም ከአፍሪካ ቀዳሚ የአየር ኃይል የመኾን ራዕይ ሰንቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት ቀደም ባሉት ዓመታት በፖለቲካ አመለካከት እና በብሔር ማንነት ተከፍለው አየር ኃይሉ ችግር ውስጥ ወድቆ እንደነበረ አስታውሰዋል፡፡

ከለውጡ በኋላ ግን ይሄንን አስተሳሰብ በመቀየር የሠራዊት አባል ኹሉ ከፖለቲካና ከብሔር አስተሳሰብ እንዲወጣ በማድረግ ኢትዮጵያዊ መልክ ያለው አየር ኃይል መገንባት ተችሏል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ያላትን የተለያየ መልከዓ ምድራዊ አቀማመጥና የተለያየ አየር ጸባይ መቋቋም የሚችል ሠራዊት መገንባት የሚያስችል ጸጋ ያላት ሀገር መኾኗንም አንስተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም የኢፌዴሪ አየር ኃይል “ለታላቅ ሀገር ታላቅ የአየር ኃይል” በሚል መሪ ሐሳብ የዘመኑን ቴክኖሎጂ የሚረዳ የሰው ኃብት፣ ዘመናዊ ትጥቆችና የውጊያ መሠረተ ልማት አሟልቷል ነው ያሉት፡፡

ሌተናል ጀነራሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል የአየር ክልሉን ከማንኛውም ጥቃት መጠበቅና መከላከል የሚያስችል የተሟላ ቁመና ላይ መኾኑን አረጋግጠዋል፡፡

ሠራዊቱ የኢትዮጵያን የአየር ክልል 24 ሰዓት ሙሉ በተጠንቀቅ እየጠበቀ መኾኑን የገለጹት ሌተናል ጀነራል ይልማ፤ አየር ኃይሉ በማንኛውም ሁኔታ ለግዳጅ ዝግጁ የኾነ ኃይል ነው ብለዋል፡፡

በዚህም ሠራዊቱ በየቀኑ የመሳሪያ፣ የአካልና የዕውቀት ፍተሻ በማድረግ የተሟላ ሥነ-ልቦና ተላብሶ ሀገሩን እየጠበቀ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼

ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleጠመዝማዛው ወንዝ በጠመዝማዛ መንገድ!
Next article“ዓባይ የእኛ የፈጠራ ውጤት ሳይኾን የፈጣሪ ስጦታ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)