
ነሐሴ ዐ5/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የታላቁ ህዳሴ ግድብ 2ኛ ተርባይን ኃይል ማመንጨት መጀመሩ የኢትዮጵያን የኀይል ፍላጎት ከሟሟላት ባሻገር ለግብጽና ሱዳን በቂና የተመጣጠነ ውኃ የማግኘት ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ ወሳኝ ምዕራፍ መኾኑን የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ምሁራን አስታወቁ።
የዩኒቨርስቲው ምሁራን የህዳሴ ግድብ 2ኛ ተርባይን ዛሬ ኃይል ማመንጨት መጀመቱን በማስመልክት ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የውኃ ሀብት ምኅንድስና ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር ሞልቶት ዘውዴ ሀገሪቱ ትልቅ ወጀብ ውስጥ ኾና የግድቡ ግንባታ ሳይስተጓጎል በተያዘለት ሂደት መከናወኑ ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል።

2ኛው ዙር ተርባይን ኀይል ለማመንጨት መብቃቱን የሚያበስረው ዜና ዛሬ በመሰማቱ ዜጎች ቀሪዎቹም ተርባይነሮች ተጠናቀው ወደ ሥራ ይገባሉ የሚል ተስፋ እንዲኖራቸው ያደርጋል ነው ያሉት።
የህዳሴው ግድብ የኀይል ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር ለታችኞቹ ሀገራት በቂና የተመጣጠነ የውኃ ፍሰት እንዲኖር የሚያስችል ግዙፍ ፕሮጀክት መኾኑን ጠቅሰዋል።
በተለይ ኀይል አመንጭቶ ከግድቡ የሚወጣው ውኃ ከደለል በጸዳ መልኩ የተጣራ በመኾኑ የሱዳንና የግብጽ ግድቦችን የአገልግሎት ዘመን የሚያራዝም ነው ብለዋል።
የግድቡን ዘላቂ አገልግሎት ለማረጋገጥ በግድቡ ተፋሰሶች የእጽዋት ልማት፣ የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራ ላይ መረባረብ እንደሚያስፈልግ ተባባሪ ፕሮፌሰር ሞልቶት ገልጸዋል።
በግድቡ ዙሪያ መንግሥት እየተከተለ ያለው ጠንካራ የዲፕሎማሲ ሥራም የሚደነቅ መኾኑን ተናግረዋል።
በዩኒቨርስቲው የውኃ ሀብትና መስኖ ምኅንድስና ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ቴዎድሮስ አሰፋ በበኩላቸው እንደ ሀገር በ2014 ዓ.ም ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን ችግሮችን ተቋቁሟ 2ኛው ተርባይን ኀይል ማመንጨት እንዲጀመር መደረጉ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።

ግድቦች ሲሠሩ ውኃ መያዛቸው ለኛ ኀይል በማመንጨት ከሚያስገኘው ጥቅም ባለፈ ለታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ደለል ለማስቀረት እና 90 በመቶ የጎርፍ አደጋን እንደሚቀንስ ጥናቶች እንደሚያሳዩ አስረድተዋል።
ዛሬ ኃይል ማመንጨት የጀመረው ተርባይን ወደ ሀገሪቱ የኃይል ማሰራጫ ሲስተም ውስጥ ሲገባ አሁን ላይ የሚታየውን የኀይል መቆራረጥ ችግር በመቅረፍ ረገድ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አውስተዋል።

በቀጣይም የግድቡ ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ሥራ ሲጀምር ንጹሕ፣ ዘላቂነት ያለውና በዝቅተኛ ዋጋ ለጎረቤት ሀገራት ጭምር የኤሌክትሪክ ኃይል በሽያጭ በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን ለማጎልበት እንደሚያስችል ዶክተር ቴዎድሮስ አብራርተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
