“የሕዳሴ ግድቡን ለማስተጓጎል የተደረጉ ፈተናዎችን ሙሉ በሙሉ በማለፍ የፕሮጄክት ሥራው ቀጥሏል” የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ

143

ባሕር ዳር: ነሐሤ 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ተርባይን ኀይል ማመንጨት ጀምሯል፡፡ በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ በሁለት ተርባይኖች ኀይል ለማመንጨት ዕቅድ ተይዞ ማሳካት መቻሉን ገልጸዋል፡፡ ሦስተኛው ሙሌት በሂደት ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

የመካከለኛውን የግድብ ከፍታ 100 ሜትር ማድረስ መቻሉንም ገልጸዋል፡፡ የግድቡን ግራና ቀኝ ከፍ በማድረግ ሦስተኛው ሙሌት በሂደት ላይ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት፡፡

የሲቭል ሥራዎች ግንባታ 95 በመቶ መድረሱንም አስታውቀዋል፡፡

የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራ እና ተከላ 61 በመቶ፣ የውኃ መስተላለፊያ የብረታ ብረት ሥራዎችን 73 በመቶ በማድረስ የፕሮጄክቱ አጠቃላይ አፈጻጸም 83 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱንም አስረድተዋል፡፡ በቀጣይ ሁለት ተኩል ዓመታት ግድቡን ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ታቅዶ እየተሠራ መኾኑንም አስታውቀዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ በውጭም ሆነ በውስጥ የተፈተነችበት ጊዜ እንደኾነ ያነሱት ኢንጂነር ክፍሌ የፕሮጄክቱን ሥራ ለማሰናከል ከፍተኛ ርብርብ መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡

በመንግሥት ሙሉ ድጋፍና ክትትል ፈተናውን በሙሉ በማለፍ የፕሮጄክቱ ግንባታ ሳይስተጓጎል በሚያስደንቅ ሁኔታ መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሳይስተጓጎል እንዲቀጥል ላደረጉ ሁሉ ሥራ አስኪያጁ አመስግነዋል፡፡

በታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የአባቶቻችን ትልምና ፍላጎት በማሳከት ሀገርን በጸና መሠረት ላይ ማቆም የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር)
Next articleየውጭ ዜጎችን ምዝገባ ማራዘሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።