
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የቻይና የመከላከያ ሰራዊት የተመሰረተበትን 95ኛ አመት ክብረ በዓል በማስመልከት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የቻይና የመከላከያ ሰራዊት የሀገሩን ሉአላዊነት፣ ፀጥታና ጥቅም ከማስከበር አልፎ ለአለማችን ሰላምና መረጋጋት እያደረገ ላለው በጎ ሚና ያላቸውን አድናቆት መግለጻቸውን የመከላከያ ሰራዊት በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡
ቻይናና ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት የዘለቀ ታሪካዊ ወዳጅነት እንዳላቸው ያወሱት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ፤ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በመመስረት በሀገራቱ መካከል ያለው ግንኙነት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በባህል፣ በትምህርት እና በጤና መስኮች ከፍተኛ ዕድገት እያሳየ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡

ሁለቱ ወዳጅ ሀገራት በወታደራዊ ዲፕሎማሲና ትብብር ላይ ከፍተኛ ዕድገት ላይ እንደደረሱ የገለፁት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እየተሰራም እንደሚገኝ አረጋግጠዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
