
ወልድያ: ሐምሌ 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)ን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በራያ ቆቦ ወረዳ የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ልዩ ኀይል አባላትን አበረታተዋል።
አካባቢው አሸባሪው ትህነግ ተደጋጋሚ ትንኮሳ የሚያደርግበትና ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚጥርበት ቀጣና መኾኑን በመገንዘብ የወገን ጦር የተሰጠውን ሀገራዊ አደራ በጀግንነት ዝግጁ ኹኖ መጠበቁን አድንቀዋል።

ሽብርተኛው ትህነግ በአማራ ክልል ወረራ በፈጸመበት ወቅት መከላከያ ሠራዊት፣ አማራ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ከሕዝቡ ጋር ተቀናጅቶ ጠላትን አሳፍሮ መመለሱን ያስታወሱት ርእሰ መሥተዳድሩ አሁንም ማንኛውንም አይነት ትንኮሳ ለመመከት ሠራዊቱ ያለው ዝግጅትና ቁርጠኝነት እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ሕዝባዊ አንድነት ለማረጋገጥ መንግሥት በቁርጠኝነት እየሠራ መኾኑንም ርእሰ መሥተዳድሩ ለሠራዊት አባላቱ ገልጸውላቸዋል።
ሠራዊቱ በጥቅና በስንቅ የተሻለ እንዲኾንም መንግሥት የተቻለውን ኹሉ ጥረት ያደርጋል ነው ያሉት።
የሕዝባችሁን ክብርና ደኅንነት ለማስጠበቅ ባላችሁ ቁርጠኝነት ኮርተንባችኋል፤ በቀጣይም ጠላት የየያዛቸውን አካባቢዎች ለማስለቀቅ ትግላችን ይቀጥላል ብለዋል።

አሸባሪው ትህነግ በመንግሥት በኩል የሰላም ጥሪ ቢቀርብለትም አሁን ላይ እያደረጋቸው ያሉ እንቅስቃሴዎች ለሰላም ዝግጁ አለመኾኑን የሚያሳይ በመኾኑ በመጣበት አግባብ ታግለን የሽብር ቡድኑን ቅዠት እናከሽፍበታለን ሲሉም የሠራዊት አባላቱን አበረታተዋል።
የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች በራያ ቆቦ ወረዳ አራዶም 08 ቀበሌ ኦፍላ ተፋሰስ ተገኝተው ከሠራዊት አባላቱ ጋር ችግኝ ተክለዋል።
ዘጋቢ:- ስማቸው እሸቴ – ከራያ ቆቦ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
