
ባሕር ዳር: ሐምሌ 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሶስተኛውን የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ የእለቱ የክብር እንግዳ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ሰብሳቢና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉን አቀፍ ልህቀት ማምጣት አለባቸው ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች ለለውጥና ለሀገር ሁለንታዊ ብልጽግና ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ ነው ያሉት አቶ አደም መንግሥትም ለዩኒቨርሲቲዎች ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች ለማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንባታ ትኩረት ሰጥተው መሥራት ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት።
አቶ አደም እንደሚሉት ዩኒቨርስቲዎች የንድፈሃሳብ ልህቀት ብቻ ሳይኾን የተግባር ልህቀትም ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።
በመማር ማስተማር ፣በምርምርና በማኅበረሰብ አገልግሎት ብቻም ሳይኾን በተቋም አመራር ፣በፋይናንስ አስተዳደር ላይም ልህቀት ያስፈልጋል ሚናችሁም ከፍተኛ መኾን አለበት ሲሉም አሳስበዋል።
በተለይም በግዥና ፋይናንስ፣ በንብረት አስተዳደር ላይ ወሳኝ ሚና መጫውት እንዳለባቸው ነው የተናገሩት።
የሀገሪቱ ትላልቅ ፕሮጀክቶች የሚስተዋልባቸውን ሁሉን አቀፍ ተግዳሮት የሚፈታ ሚና መጫወትም አለባቸው ነውያሉት።
‟መንግሥት ከሚደጉማችሁ በተጨማሪ ሃብት በመፍጠርና ሃብትን በአግባቡ ማስተዳደር ላይ ልህቀት እንድታመጡ መሥራት ይጠበቅባችኋል” ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች ሀገር የሚገነቡ ሃሳቦች የሚፈልቁባቸው እንጂ ሀገር የሚያፈርሱ ሃሳቦች የሚመንጭበት እንዳይኾን መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል።
መድረኩ በፌዴራል ግዥና ንብረት ባለስልጣን እና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀ ነው።
በግዥ ሂደትና በንብረት አያያዝ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማመላከትና የመፍትሔ አቅጣጨዎችን ለማስቀመጥ ታልሞ የተዘጋጀ መድረክ ነው ተብሏል።
ዘጋቢ :-ጋሻው አደመ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
