
👉ንጉሥ ሚካኤል ቤተመንግሥታቸውን ከተንታ ወደ ደሴ በማዛወር ጀሜ በተባለው ከፍተኛ ስፍራ ላይ መሰረቱ።
ይህ ሥፍራ ከጄሜ ኮረብታ እስከ 60 ኪሎ ሜትር እርቀት ለመቆጣጠር የሚያስችል ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ቦታ ነው።
👉ከመሀል ሀገር ምፅዋ እንዲሁም ከምእራብ የሀገራችን ክፍል ወደ ታጁራ የሚያልፍን የንግድ መስመር ለመቆጣጠር የነበራቸው ፍላጎት ይህን ሥፍራ ለመቀመጫነት እንዲመርጡት ምክንያት ነበር፡፡
👉አካባቢው ውኃ እና የማገዶ እንጨት በበቂ ሁኔታ መኖሩ አካባቢው እንዲመረጥ አድርጓታል።
👉ቤተመንግሥቱ ከ10 ያላነሱ ክፍሎች ያሉት ዘመናዊ ሕንፃ ነው፡፡
👉ከቤተመንግሥቱ ቅጥር ግቢ የተለያዩ የግብር ሕንፃዎች ይገኛሉ።
👉ከነዚህም ውስጥ የንጉሡ ጽሕፈት ቤት፣ የልጅ እያሱ እልፍኝ፣ የፀሎተ ቤት፣ የችሎት ቤት፣ ግዚያዊ እስርቤት እና ፈትል ቤት ይገኙበታል፡፡
👉ዘግይቶ የተሠራው አይጠየፍ አዳራሽም የዚሁ አካል ነው።
የንጉሥ ሚካኤል ቤተመንግሥት የአስተዳደር መዋቅርና አደረጃጀት ስንመለከት እልፍኝ አስከልካይ፣ ሊቀመ ኳስ፣ ፀሐፌ ትእዛዝ፣ አዛዥ፣ ሊጋባ፣ በጅሮንድ እና ባልደራስ ይሰኛሉ፡፡
👉ደሴ ከተማ እንድትመሠረት እና እንድትሰፋ ትልቁን ሚና የተጫወተው ይሄው ታሪካዊ ቤተመንግሥት ነው።
👉የአይጠየፍ አዳራሽ ግንባታ በ1906 ዓ.ም ተጀምሮ ሥራው በ1907 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡
👉ሕንፃው በ2ሺህ 131 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ሲኾን 45 ሜትር በ27 ሜትር ስፋት ያለው ነው፡፡
👉በ10 ሜትር ቁመት በ70 ምሰሶዎች የተዋቀረ የግብር አዳራሽም ነው።
የግብር አዳራሹ ከ5 ሺህ ሰው በላይ ማስተናገድ የሚችልም ነው፡፡
👉ወደ ደሴ ጎራ ብለው ይህን ድንቅ ሥፍራ ይጎብኙ፡፡
አሚኮ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
