“ሀገራዊ የምክክር መድረክ ስኬታማ እንዲኾን በጥንቃቄና በከፍተኛ ኀላፊነት እየተሠራ ነው” ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

128

አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ የሚካሄደዉ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ስኬታማ እንዲኾን እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በጥንቃቄ እና በከፍተኛ ኀላፊነት እየተከናወነ እንደኾ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገልጸዋል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ሀገራዊ ምክክሩን ለማካሄድ በሚደረገዉ ሂደት አጀንዳዎች በመሰረታዊነት የሚለቀሙት ከልሂቃን ሳይኾን ታች ካለዉ ሕዝብ መኾኑን ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽነሩ ያልተሰሙ ድምጾች እንዲደመጡ እና አላግባባ ያሉ ጉዳዮችን ለመለየት ጥሩ አጋጣሚ የሚፈጠርበት እንደኾነ ነው ያስረዱት፡፡

ሀገሪቱ ዜጎቿ ከጊዜ ጊዜ አላግባባቸው የሚሉ ጉዳዮችን በዘላቂነት ይፈታል ያለችዉን ሀገራዊ የምክክር መድረክ ለማድረግ ቅድመ ሁኔታዎች እያከናወነች ነዉ፡፡

ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕሮፌሰር) የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤትን ከማቋቋም ጀምሮ አዋጁን በሚገባ የመረዳት፣ የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ የመመርመር ተግባር መከናወኑን አስረድተዋል፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን በየክልሎች አስፈላጊ ከሚባሉ ባለድርሻ አካላት፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ከርእሰ ብሄሯ ጋር መምከራቸዉንም አብራርተዋል፡፡

‟አለባብሰዉ ቢያርሱ በዓረም ይመለሱ እንዲኾን አንፈልግም” የሚሉት ዋና ኮሚሽነሩ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ያደረጉ የበርካታ ሀገራት ተሞክሮ እና ጥናት የሚያሳየዉ የችኮላ ተግባራቸዉ ለዉጤት እንዳላበቃቸው ነው ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ የሚካሄደዉ ሀገራዊ የምክክር መድረክም ስኬታማ ይኾን ዘንድ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በጥንቃቄ እና በከፍተኛ ኀላፊነት እየተከወነ ነዉ ብለዋል፡፡

ሀገራዊ ምክክሩን ለማካሄድ በሚደረገዉ ሂደት አጀንዳዎች በመሰረታዊነት የሚለቀሙት ከልሂቃን ሳይኾን ከሕዝብ በመኾኑ ያልተሰሙ ድምጾች ይደመጣሉ ነው ያሉት፡፡ ኮሚሽነሩ አላግባባ ያሉ ጉዳዮችን ለመለየት ጥሩ አጋጣሚ እንደኾነም ነው ያስገነዘቡት፡፡

ሀገር ታመመች ማለት ታማሚም አስተማሚም ሕዝቦቿ በመኾናቸው ሀገራዊ ምክክሩን በብስለት እና በኀላፊነት አካሂዶ ለዉጤት ለማብቃት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሃሳብ የማዋጣት እና በንቃት የመሳተፍ ሀገራዊ ገዴታዉን ሊወጣ ይገባልም ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- በለጠ ታረቀኝ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼

ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleእነኾ ስለ እውነት ሞትን ናቁት!
Next articleየንጉሥ ሚካኤል ቤተመንግሥትን በጨረፍታ።