
ባሕር ዳር: ሐምሌ 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ለክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኀላፊነት፣ ለዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር እና ለንጋት ኮርፖሬት የቦርድ አባላት እጩ ተሿሚዎችን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
ምክር ቤቱም የቀረቡ እጩ ተሿሚዎችን ተቀብሎ ሹመታቸውን አጽድቋል።
በዚህ መሠረት:-
1.አቶ እርዚቅ ኢሳ – የአማራ ክልል የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ
2. አቶ ሰውበሰው ብዙዓየሁ- የአብክመ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር ኾነው ተሹመዋል።
•ምክር ቤቱ የንጋት ኮርፖሬት የቦርድ አባላትን ሹመትም አጽድቋል።
1.አቶ ስዩም መኮንን -የንጋት ኮርፖሬት የቦርድ ሰብሳቢ
2.ወይዘሮ ዓይናለም ንጉሤ-የንጋት ኮርፖሬት ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ
3.ዶክተር ስንታየሁ ወልደ ሚካኤል-አባል
4.ዶክተር አሕመዲን አሕመድ-አባል
5.ዶክተር ጥላሁን መሐሪ -አባል
6.ዶክተር አሥራት አጸደወይን-አባል
7.አቶ አርማዬ ገላው -አባል
8.ወይዘሮ ባንች አምላክ ገብረ ማሪያም-አባል
9.ዶክተር ጋርዳቸው ወርቁ-አባል ኾነው ተሹመዋል።
ዘጋቢ:-ጋሻው አደመ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/