ሩስያ “ብድር ለልማት” በሚል ፓኬጅ የኢትዮጵያ መንግሥትን የልማት ጥረት ለመደገፍ ወስናለች” ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

120

አዲስ አበባ: ሐምሌ 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በሳምንታዊ መግለጫ እንደገለጹት ሩስያ ከቀድሞዋ ሶቭየት ሕብረት ዘመን ጀምሮ ሲንከባለል የቆየ ቀሪ ብድር “ብድር ለልማት” በሚል ፓኬጅ በመለወጥ የኢትዮጵያ መንግሥትን የልማት ጥረት ለመደገፍ ሩስያ መወሰኗን አስታውቀዋል።
የሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ ውጤታማ ጉብኝት ማድረጋቸውን ቃለ ዐቀባዩ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እና ሩስያ አሁን ላይ ያላቸውን መልካም የሚባል የፖለቲካ ግንኙነት በኢኮኖሚ፣ ንግድ፣ ግብርና እና በኃይል አማራጮች ማስፋት ይገባቸዋል ብለዋል።
ከፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ እና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በኹለትዮሽ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውንም ቃል ዐቀባዩ ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ሽመልስ ዳኜ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article❝የአትሌቲክስ ቡድኑ የተቀዳጀው ድል ኢትዮጵያ በአንድነትና በፅናት ፈተናዎቿን እንደምታሸንፍ ያሳየ ነው❞ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ
Next articleየአማራ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ።