
ሐምሌ 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሜዳሊያ ብዛት ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዛ በድል እንድታጠናቅቅ ያደረገው የአትሌቲክስ ቡድን ወደ ሀገሩ ገብቷል።
የአትሌቲክስ ቡድኑ ዛሬም በአዲስ አበባ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ታሪክ በዓለም አደባባይ ስሟ በጉልህ እንዲነሳ፣ ሰንደቅ ዓላማዋ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ካደረጉ አንጋፋ አትሌቶች አንዱ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ነው።
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ለአትሌቶቹ እየተደረገ ባለው አቀባበል ተገኝቶ ለጋዜጠኞች በሰጠው አስተያየት፤ የአትሌቶቹ ድል ትልቅ ትርጉም እንዳለውና በተገኘው ውጤት ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው ተናግሯል።
በተለይ ኢትዮጵያ ስሟ በጦርነትና በተለያዩ ችግሮች እየተነሳ ባለበት በዚህ ወቅት የአትሌቲክስ ቡድኑ የተቀዳጀው ድል፤ ኢትዮጵያ በአንድነትና በፅናት ፈተናዎቿን እንደምታሸንፍ ያሳየ ነው ብሏል።
በጥቅሉ ለተገኘው ድል የድሉ ባለቤቶችንም ፈጣሪንም ማመስገን እንደሚገባም አትሌት ኃይሌ ተናግሯል።
አትሌት ኃይሌ መላው ኢትዮጵያዊ በድሉ የተደሰተው ባገኘነው ወርቅ፣ ብርና ነሐስ ብቻ ሳይኾን፤ የአትሌቲክስ ቡድኑ አባላት በዓለም አደባባይ ባሳዩት ኢትዮጵያዊ አንድነትና ሕብረት ነው።
አትሌቶቹ ያሳዩትን አንድነት፣ ሕብረትና ትብብር በሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመድገም ኹሉም ኢትዮጵያዊ ለእናት ሀገሩ ሰላምና ልማት በአንድነት ሊነሳ እንደሚገባ መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።
”ይህን ትብብር ወደ ፖለቲካው፣ ወደ ኢኮኖሚውና ለሌሎች በጎ ነገሮች በማዋል ኢትዮጵያ ፍቅርና አንድነት የሰፈነባት ሀገር ማድረግ ይገባል” ነው ያለው።
ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው አራት የወርቅ፣ አራት የብርና ሁለት የነሐስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ታሪካዊ ድል አስመዝግባለች።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
3 Comments