በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው የመረጃ ጦርነት በሳይበር ደህንነትና ሌሎችም ተቋማት የጋራ ጥረት እየተመከተ ነው- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

152

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 19/2014 (አሚኮ) በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው የመረጃ ጦርነት በሳይበር ደህንነትና ሌሎችም ተቋማት የጋራ ጥረት እየተመከተ መኾኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ የተከፈተባትን የተቀናጀ ግራጫ ጦርነት እየተፋለመች መኾኗን መግለፃቸው ይታወሳል።

በመኾኑም መንግሥት ጦርነቱን ለመመከትና ህግ ለማስከበር እየሞከረ መሆኑን ጠቅሰው፤ እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተገናኘ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሣ ቴክኖሎጂን በመጠቀምና ትክክለኛ ፈጣን መረጃን ወደ ሕዝብ በማድረስ የመረጃ ጦርነቱን ለመመከት ስልት መነደፉን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ጠላቶች በሀሰተኛ መረጃ ሕዝቡን ለመከፋፈል የተለያዩ ጥረቶችን እያደረጉ መኾኑን ጠቅሰው የመረጃ ጦርነቱ አገር ለማፍረስ ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦለት በተቀናጀ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን አብራርተዋል።

በመኾኑም በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው የመረጃ ጦርነት በሳይበር ደህንነት ተቋማትና ሌሎችም የጋራ ጥረት እየተመከተ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

መንግሥት የጠላትን የመረጃ ጦርነት ለመመከት ተቋማትን በማጠናከር ላይ መሆኑንም ጠቁመው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነትን የመሳሰሉ የመረጃ ደህንነት ተቋማት በመቀናጀት በልዩ ትኩረት እየሠሩ ስለመሆኑም ተናግረዋል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የመረጃ ትክክለኛነትን ማጣራት፣ ወደ ህዝብ ፈጣን መረጃን ማድረስና አጀንዳ መቅረፅ ላይ የበኩሉን ሚና እየተወጣ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ የመረጃ ጦርነቱን በመመከት ሂደት የመገናኛ ብዙሃንም የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼

ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበአማራ ክልል የግብርና ምርትን በእጥፍ ለመጨመር ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ መኾኑን የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ገለጹ፡፡
Next articleታሪካዊ ድል ያስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ነገ አዲስ አበባ ይገባል።