“የዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት መሥራት ይገባል” የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ

122

ባሕር ዳር: ሐምሌ 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት መሥራት እንደሚገባም ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ተናግረዋል።
በአማራ ክልል ምክር ቤት በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ሥራዎችን እያቀረቡ የሚገኙት ርእስ መስተዳድሩ በበጀት ዓመቱ ለ723 ሺህ 693 ዜጎች በቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን አስታውቀዋል።
የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የምጣኔ ሀብት ችግር ለመፍታት 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር መሠጠቱንም አብራርተዋል።
የዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት መሥራት እንደሚገባም አመላክተዋል።
በክልሉ የሚገኙ ማዕድናትን በጥናት መለየት፣ ለማዕድን ልማት ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣ የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት፣ የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት በተግባር የተመሠረቱ ሥራዎችን ለመሥራት ጥረት መደረጉንም አመላክተዋል።
በተደረገው የማዕድን ጥናት በክልሉ ልዩ ልዩ ማዕድናት ግኝቶች መገኘታቸውን ነው የተናገሩት። በክልሉ ሰባት የሲሚንቶ ፋብሪካ ለመገንባት የምርምራ ፈቃድ የተሰጣቸው መሆኑንና ሁለቱ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀው ወደ ምርት ፈቃድ ደረጃ መድረሳቸውን አስታውቀዋል።
ጥቅማቸው ከፍ ያሉ 13 የድንጋይ ከሰል፣ 8 የወርቅ ምርመራ፣ 12 ልዩ አነስተኛ የወርቅ ምርት እና የብረት ምርመራ ፈቃድ መሰጠቱን ተናግረዋል። ለዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶ ይደገፋልም ብለዋል።
የልማት ፕሮጄክቶች እየተገነቡ መሆናቸውንም አስታውቀዋል። የንፁህ መጠጥ ውኃ ተደራሽነት ለመጨመር መሠራቱንም ተናግረዋል። የኤሌክትሪክ ኃይልና የመንገድ ተደራሽነትን ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑንም አመላክተዋል።
ከተሞች በፕላን እንዲመሩና ፅዱና ማራኪ እንዲሆኑ ለ54 ከተሞች መሠረታዊ ካርታ፣ ለ12 ከተሞች መዋቅራዊ ፕላን ተዘጋጅቷልም ነው ያሉት።
በከተሞች የሚታየውን ችግር ለመፍታት ጥረት ይደረጋልም ብለዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የአማራ ሕዝብ ሀገርን ለማፅናት በአንድ እጁ እርፍ በሌላ እጁ ነፍጥ ይዞ ጠላቶቹን የሚታገል ኩሩና ጀግና ሕዝብ ነው” አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ
Next articleበአማራ ክልል የግብርና ምርትን በእጥፍ ለመጨመር ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ መኾኑን የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ገለጹ፡፡