“የአማራ ሕዝብ ሀገርን ለማፅናት በአንድ እጁ እርፍ በሌላ እጁ ነፍጥ ይዞ ጠላቶቹን የሚታገል ኩሩና ጀግና ሕዝብ ነው” አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ

217

ባሕር ዳር: ሐምሌ 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን እያከሄደ ነው። በጉባዔው መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባዔ ያለ ወንጀላቸው በግፍ ለተጨፈጨፉት እና የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ ሲሉ ለተሰዉ የፀጥታ ኃይሎች የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።

መንግሥት የጀመረውን የሕግ ማስከበርና በጥፋተኞች ላይ እየወሰደ ያለውን ርምጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያ ያለችበት ጉዜ በመገንዘብ መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ በርካታ ጠላቶች እንዳሉባት ያነሱት አፈ ጉባዔዋ የውጭ ጠላቶች የውስጥ ባንዳ በመግዛት በዘርና በብሔር ለማከፋፈል እየሠሩ መሆናቸውንም ገልፀዋል። ጠላቶች ኢትዮጵያን ለመበተን እየሠሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ባንዳዎችን እና አሸባሪዎችን በግልጽ መታገል እንደሚገባ ነው የተናገሩት። የአማራ ሕዝብ በፍትሕ እንደሚያምን ተናግረዋል። ጠላቶች የአማራን ሕዝብ ታሪክ በማዛባት በሀገሩ ተረጋግቶ እንዳይኖር እያደረጉት መሆናቸውንም ገልሕዋል። የአማራ ሕዝብ በምንም ሁኔታ ሆኖ በኢትዮጵያ ጉዳይ የማይደራደር መሆኑንም አንስተዋል።

የአማራ ሕዝብ ሀገርን ለማፅናት በአንድ እጁ እርፍ በሌላ እጁ ነፍጥ ይዞ ጠላቶቹን የሚታገል ኩሩና ጀግና ሕዝብ መሆኑን አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ገልጸዋል።

የሕዝቡን የመልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

በክልሉ አሁንም በአሸባሪ ቡድኖች ተፈናቅለው ተገቢ ባልሆነ አያያዝ የሚገኙ ዜጎች መኖራቸውንም ገልጸዋል። ዜጎችን በዘላቂነት የማቋቋሙ ጉዳይ በትኩረት ሊሠራበት እንደሚገባም አሳስበዋል።

የኢፌዴሪ መንግሥት እያደረገ ባለው የሰላም አማራጭ ጥረት የአማራ ክልል ምክር ቤት በጋራ እንደሚሠራም ገልጸዋል። የሰላም አማራጭ በአንድ ወገን ብቻ አይገኝም ያሉት አፈ ጉባዔዋ አሁንም ግልፅ የሆኑ ትንኮሳዎች እየተደረጉ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ሕዝቡ ለዳግም ወረራ እንዳይጋለጥ በቂ ዝግጅት ሊደረግ ይገባልም ብለዋል።

የአማራ ክልል ከሌሎች ክልሎች ጋር እያደረገ ያለውን መልካም ተሞክሮ አጠናክሮ መቀጠል አለበትም ብለዋል።

በሕዝብ ሃብት ላይ በአቋራጭ ለመበልጸግ በሚሞክሩ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ አስፈላጊውን ርምጃ መውሰድ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበኩር ጋዜጣ – ሐምሌ 18/2014 ዓ.ም ዕትም
Next article“የዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት መሥራት ይገባል” የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ