“የወልቃይትና ራያ ማንነት የክልሉ መንግሥት የማይቀየር አቋም ነው” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)

1143

ደሴ፡ ሐምሌ 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ከደሴ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ የንጹሃን አማራዎች በወለጋና ሌሎች አካባቢዎች እየደረሰባቸው ያለው የግፍ ጭፍጨፋን የክልሉ መንግሥት እንዴት ሊያስቆም አስቧል የሚሉና የወልቃይትና ራያ ማንነት ጉዳይን በተመለከተ ከነዋሪዎች ጥያቄዎች ተነስተዋል።
ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ከነዋሪዎች ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ የአማራን ሞት ለማስቀረት በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ ችግሩን መቅረፍ የሚችሉ አካላት ጋር መሥራትና የሕዝባችንን ህመም ሰምተን ያለብንን ድርብ ኀላፊነት ለመወጣት ቀን ከሌት እንሠራለን ብለዋል።


ሕዝቡን የሚያስቆጨው የወገኖች መጨፍጨፍ የክልሉን መንግሥትም ይሰማዋል ለዚህ ችግር ዘላቂ መፍትሄ የምናመጣው ከሕዝባችን ጋር በጥምረት ስንሠራ ስለሆነ ከገባንበት ፈተና በጋራ መሥራት አለብን ብለዋል ርእሰ መስተዳድሩ። “የአማራ ሕዝብ ሞት ቢያመንም መፍትሄው ጊዜያዊ ጩኸት ባለመሆኑ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ከሕዝባችን ጋር እንሠራለን” ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ፡፡
ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሠሩ ያሉ ኃይሎች በአማራና ኦሮሞ ሕዝቦች መካከል አለመግባባት እንዲፈጠር ማድረግ ስላለባቸው ንጹሃን አማራዎች በተለያዩ አካባቢዎች በግፍ እየተጨፈጨፉ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ይህን የጠላት ዓላማ ለማክሸፍም በከፍተኛ ትኩረት እየሠራን ነው ብለዋል፡፡ ይህ ማለት ግን የወገኖቻችን ሞት አያመንም ማለት እንዳልሆነ ልንገነዘብ ይገባል ብለዋል ዶክተር ይልቃል። ኢትዮጵያን ከመፍረስ ለመታደግም የገጠመንን ፈተና በዘላቂነት ለመሻገር ከፌዴራል መንግሥት ጎን አየተሠራ መሆኑንም አንስተዋል።

የወልቃይትና ራያ ማንነት የክልሉ መንግሥት የማይቀየር አቋም ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ራያና ወልቃይት ሕዝቡም አማራ መሬቱም የአማራ ነው እነዚህን ቦታዎች ለማንም አሳልፈን አንሰጥም ብለዋል።
የአማራ ሕዝብና የክልሉ መንግሥት ሰላም ፈላጊ መሆኑን የገለጹት ርእሰ መሥተዳድሩ ሰላም ፈላጊዎች ብንሆንም የጠላትን ወረራ ለመመከት ግን ሁሌም ዝግጁ ነን የጠላትን ወረራ መመከት የሚያስችል አስተማማኝ ቁመና ላይም እንገኛለን ብለዋል።
ዘጋቢ፡-አሊ ይመር
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleʺድል ለእርሷ ተሰጥቷል፣አሸናፊነት ከእርሷ ጋር ተሰርቷል”
Next articleበኩር ጋዜጣ – ሐምሌ 18/2014 ዓ.ም ዕትም