
አዲስ አበባ: ሐምሌ 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 5 ሺህ 58 ተማሪዎችን አስመርቋል።
ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የምረቃ ሥነ- ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር መማር ማለት የባህሪ ለውጥ ማምጣት ነው፤ ተመራቂዎች በዘር፣ በሃይማኖት ከመከፋፈል ወጥተው ለሀገር የሚጠቅም ሥራ እንዲሠሩና የገጠመንን ችግር በአንድነት መመከት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
❝ኢትዮጵያን ባላችኹበት ኾናችሁ ልክ እንደ ቀደሞ አባቶችና እናቶቻችሁ ውደዷት፣ ያገናችሁትን ዕውቀት ወደ ሥራ በመለወጥ ሀገሪቱ የገጠማትን ችግር እንድታቃልሉና በሙያችሁ ሕዝባችሁን በፍፁም እኩልነት እንድታገለግሉ አደራ እላለሁ❞ ብለዋል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ላለፉት 72 ዓመታት በማስተማርና ምርምር በማድረግ ኢትዮጵያን ሲያገለግል ቆይቷል። በግብርናው፣ ኢንዱስትሪዎችና ሌሎች ዘርፎች የሚፈልጉትን የተማረ የሰው ኀይል በጥራት ሲያቀርብ ቆይቷል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ በርካታ ችግር እያስተናገደች ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ፣ ሀገር ለማሳደግ መረባረብ ሲገባ የበርካታ ንጹሐን ደም እየፈሰሰ ነው። ሕዝባችን የሚፈልገው በሰላም ሠርቶ በሰላም መግባት ነው፣ መሠረተ ልማቶች እንዲሟሉለት ነው።
ሀገራቱ ከጦርነት፣ ከስጋት፣ ከመፈናቀል ወጥታ ወደ ተሻለ ደረጃ እንድትደርስ መንግሥት የተለያዩ እቅዶችን ቀርጾ እየሠራ መኾኑን ጠቅሰው የተማረ ሰው ችግር ውስጥ ያለን ሕዝብ ከችግር ማውጣት እንዳለበት አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሐና፣ ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ወቅት 11 የምርምር ተቋማትና ኹለት የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አሉት። ከ40 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያሰተማረ ነው። 40 በመቶ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ሲኾኑ 33 በመቶው ደግሞ ሴቶች ናቸው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከውስጥና ከውጭ ጠላት በበዛባት ወቅት እናንተን ተንከባክባ ለዛሬው ቀን አብቀታኋለች፣ በዘርና በጎሳ ከመከፋፈል ወጥታችሁ ሀገሪቱን በጥናትና ምርምር መርዳት ይገባችኋል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/