በወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ እየተመራ የሀገሩን ክብር የሚጠብቅ ሠራዊት መገንባቱን የማዕከላዊ ዕዝ ገለጸ።

300

ባሕር ዳር: ሐምሌ 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የማዕከላዊ እዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ ሠራዊቱ በየጊዜው በሚሠጠው ስልጠና አቅሙን እየገነባ፣ መሬትን በካርታ እያነበበ፣ አስቸጋሪ መልካ ምድርን እና የአየር ፀባይን ተቋቁሞ የሚሰጠውን ማንኛውንም ግዳጅ ለመፈፀም ዝግጁ ነው ብለዋል።

ውትድርና የብዙ የእውቀት መሸመቻ ቦታ እንደኾነ የተናገሩት ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ “ወታደር ድል ሊቀዳጅ ከኾነ ወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ ከዕውቀት ጋር ቀምሮ መተግበር ያስፈልጋል” ብለዋል።

ለዚህ ሲባልም በማዕከላዊ እዝ ውስጥ በልዩ ልዩ ወታደራዊ ስልጠናዎች ያለፈ ምርጥ አዋጊና ተዋጊ መፍጠር እንደተቻለ ሌተናል ጀነራሉ መግለጻቸውን ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ከኅሊና ጓዳ ተስጦ የሚኖር፣ ሀገርም ጥላ ነው ቅር ቢሉት የማይቀር”
Next article“ተመራቂዎች ያገኙትን ዕውቀት ወደ ሥራ በመለወጥ የገጠመንን ችግር በአንድነት መመከት ይገባል” ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ