
አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያን ለማፍረስ አሸባሪው ትህነግ ጦርነት በከፈተበት ወቅት ሀገራቸውን ለመታደግ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩት የሄርሜላ አረጋዊ እናት ፕሮፌሰር ሃረገወይኒ አሰፋ ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ የትግራይ እናቶች ካለፈው 50 ዓመት የጦርነት ታሪክ ወጥተው ስለ ስላም ለልጆቻቸው ሊሰብኩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው ትህነግ ላለፉት 50 ዓመታት በሕዝቦች መካከል ጥላቻ፣ መከፋፈል እንዲፈጠር፣ የሰው ሂወት እንዲጠፋ እና ንብረት እንዲወድም በማድረግ ሀገርን ለማፍረስ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ነው ያስረዱት፡፡
ፕሮፌሰር ሃረገወይኒ እንደሚሉት የትግራይ ሕዝብ ልጆቹን ገብሮ መከራና ጉስቁልና ውስጥ እንዲወድቅ ኾኗል፡፡ ዛሬም እናትን ያለ ጧሪ ለማስቀረት እና ሕዝብ ወደ ኋላ እንዲመለስ ታላቅዋን ትግራይ እንመሰርታለን እያሉ የማይኾን ተስፍ ለሕዝቡ እንደሚሰጡት ነው የተናገሩት፡፡ በስልጣን በነበሩበት ዘመንም ለሕዝቡ ምንም የጠቀሙት ነገር እንደሌለ አስገንዝበዋል፡፡
ለኢትዮጵያ መፍረስ ሌት ከቀን የሚሠራው አሸባሪው ትህነግ እንደመተማመኛ የሚያደርገው የክልሉን ሕዝብ በጉያው አቅፎ እንደኾነ ነው የገለጹት፡፡ ፕሮፌሰር ሀረገወይን ዛሬም አሸባሪው ትህነግ በኢትዮጵያ ላይ እያደረሰ ላለው የክፋት ዶፍ ሕዝቡ ተጠያቂ ሊኾን እንደሚችል ሊገነዘብ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡
ሕዝቡ ባሳለፈው የግማሽ ምዕተ ዓመት የጦርነት ታሪክ ውስጥ ያተረፈው ድህነትን ነው ያሉት ፕሮፌሰር ሃረገወይኒ አሁንም ሕዝቡ ጠላት እንደሌለው አውቆ ጦርነት ይብቃን ብሎ ወደ ሰላም ፊቱን ሊያዞር ይገባል ነው ያሉት፡፡ የትግራይ እናቶች ቃታ መሳብ ትርፉ ኪሳራና መጥፎ ጠባሳ መተው እንደኾነ ተረድተው ልጆቻቸውን ስለሰላም ሊሰብኩ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
ዘጋቢ፡-ዳዊት ከበደ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/