የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የጋራ ኮሚሽን ስብስባ ሊካሄድ ነው።

159

ባሕርዳር፡ ሐምሌ 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በቅርቡ ለማካሄድ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
41ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ በዛምቢያ ሉሳካ እየተካሄደ ይገኛል።
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑካን ቡድን በስብሰባው በመሳተፍ ላይ ነው።
አቶ ደመቀ ከስብሰባው ጎን ለጎን ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ተጠባባቂ ሚኒስትር ባላል መሐመድ ኦስማን በሁለትዮሽና የአፍሪካ ቀንድ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
መንግስታት በትብብር የሚሰሩባቸው በርካታ መስኮች አሉ ያሉት አቶ ደመቀ አገራቱ በፀረ-ሽብር ዘመቻ ላይ ያላቸውን እንቅስቃሴ ማጠናከር እንደሚገባ አመልክተዋል።
የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ተጠባባቂ ሚኒስትር ባላል መሐመድ ኦስማን በበኩላቸው አዲሱ የሶማሊያ መንግስት በአገሪቱ ሰላምን ለማስፈን ልዩ ትኩረት መስጠቱንና በዚህም አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራት ትቀጥላለች ብለዋል።

አልሸባብ የሽብር ቡድንን ለማጥፋት በሚደረገው እንቅስቃሴ የሁለቱ ሃገራት ሕብረት መጠናከር እንዳለበትም ገልጸዋል።
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የሁለትዮሽ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ በቅርቡ ለማካሄድ ስምምነት ላይ መደረሱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ትናንት የተጀመረው 41ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ዛሬ ይጠናቃል።
ኢትዮጵያና ሶማሊያ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር እ.አ.አ በ2018 የጋራ ኮሚሽን ማቋቋማቸው የሚታወስ ነው።
ሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን እ.አ.አ 1961 መጀመራቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ሀገራዊ ምክክሩ ለኢትዮጵያውያን የተያዘ ኢትዮጵያዊ ሂደት ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡
Next articleየትግራይ እናቶች ባለፈው የግማሽ ምዕተ ዓመት የጦርነት ታሪክ ውስጥ ያተረፉት ድህነት መኾኑን ተረድተው ለልጆቻቸው ሰላምን ሊሰብኩ እንደሚገባ ሃረገወይኒ አሰፋ (ፕ.ር) ተናገሩ፡፡