“ሀገራዊ ምክክሩ ለኢትዮጵያውያን የተያዘ ኢትዮጵያዊ ሂደት ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

247

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላት ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተነጋግረዋል ፡፡
የኮሚሽኑ ሰብሳቢ መስፍን አርአያ (ፕ.ር) በዚሁ ወቅት ኮሚሽኑ ባለፉት አራት ወራት ያከናወናቸውን ተግባራት ለፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አብራርተዋል፡፡
በዚህም አካታችነት ፣የሀገራዊ ምክክሩና አጠቃላይ የኮሚሽኑ ሥራዎች የሚመራበት ቀዳሚ መርሆ መኾኑን ተናግረዋል፡፡
ግልጸኝነት፣ ታማኝነትና አሳታፊነትን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዮችም በመርሆዎቹ ወስጥ መካተታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ኮሚሽኑ ባለፉት አራት ወራት ረቂቅ የስትራቴጂክ ዕቅድን ጨምሮ ለምክከር ሂደቱ መሰረታዊ የንድፍ ተግባራትን ማዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪ ከቁልፍ ባለድርሻ አካላት፣ ከክልል መስተዳድሮችና ሌሎች አካላት ጋር መወያየታቸውን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽኑ በአሁኑ ወቅት የዝግጅት ምዕራፉ ውስጥ እንደሚገኝም ኢዜዘ ዘግቧል፡፡ በተያዘው ክረምት የዝግጅት ምዕራፉን እንደሚያጠናቀቅም ተመላክቷል፡፡
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በበኩላቸው በኮሚሽኑ ላይ የተጣለው ኃላፊነትና ተስፋ ከፍተኛ መሆኑን በመጠቆም ዓባላቱ በርካታ ስራዎች ከፊታቸው እንደሚጠብቋቸው ተናግረዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleዜና መጽሔት ባሕር ዳር: ሐምሌ 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ)
Next articleየኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የጋራ ኮሚሽን ስብስባ ሊካሄድ ነው።