የፌዴሬሽን ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው ።

368

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
ምክር ቤቱ ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ በግፍ ለተጨፈጨፉ ንጹሀን ዜጎች የህሊና ጸሎት በማድረግ ጉባኤውን የጀመረ ሲሆን÷ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባኤን መርምሮ በማጽደቅ ውይይቱን ቀጥሏል።
በቀጣይም የአራቱን ቋሚ ኮሚቴዎች እና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤን የ2014 ዓ.ም የአፈጻጸም ሪፖርቶች፣ ከሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባኤ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በተባሉ የውሳኔ ሐሳቦች፣ የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም በሚል ውሳኔ በተሰጣቸው እና ለምክር ቤቱ በይግባኝ በቀረቡ አቤቱታዎች ላይ በመወያየት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 1261/ 2013 ለማስፈጸም የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ፣ ውስን ዓላማ ያላቸው የድጎማ በጀትና የፌዴራል መሠረተ ልማት ስርጭት ፍትሐዊነት የክትትል ሥርዓትን ለማስፈጸም የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የተለያየዩ ሹመቶችን እንደሚያጸድቅም ተጠቁሟል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የጨለማው ልዑላን ኢትዮጵያን ለማተራመስ ዘርን መሰረት አድርገው የታጠቁ የሽብር ቡድኖችን እየተጠቀሙ ነው” አሜሪካዊው የአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ተንታኝ ሎውረንስ ፍሪማን
Next article“እስከ አሁን ከአረብ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ከታሰበው 102 ሺህ ዜጎች መካከል ግማሽ ያህሉን መመለስ ተችሏል” ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር