
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ዕዝ የሚገኝ ክፍለ ጦር ለሚሰጠው የትኛውም አይነት ግዳጅ ዝግጁ የሚያደርግ ስልጠናዎችን በማድረግ ወታደራዊ ዝግጁነቱን ከፍ ማድረጉን የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ገልፀዋል።
የተለያዩ ስልጠናዎችን በተለያዩ የመሬት ገፆችና የአየር ፀባይ ሲያካሒዱ ስለመቆየታቸው የተናገሩት የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ብ/ጀኔራል አዘዘው መኮንን፤ ያሳለፍናቸውን የጦርነት ጊዜያት መነሻ ባደረገ መልኩ ሁለንተናዊ የዝግጅት ስራዎችን ሰርተናል ብለዋል፡፡
የመከላከያ ሰራዊት ሀገርን ለማተራመስ የሚቋምጡ ኃይሎችን ለመደምሰስ በከፍተኛ ሞራል ላይ ይገኛል ያሉት ዋና አዛዡ፤ የክፍለ ጦሩ አባላትም በአሸባሪዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ በከፍተኛ ዝግጁነት ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/