“በየአቅጣጫው የተከፈተብንን ጥቃት ማክሸፍ የምንችለው መደማመጥና መተባበር ስንችል ብቻ ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)

289

ደብረ ብርሃን፡ ሐምሌ 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል (ዶ/ር) ከሰሜን ሸዋ ዞን የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር በደብረ ብርሃን ከተማ እየተወያዩ ነው።

እየተካሄደ ባለው ውይይት ንግግር ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድሩ የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ በርካታ ጥቃቶች እየተፈፀመበት ነው ብለዋል። ይህ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት ማክሸፍ የሚቻለው በመደማመጥና በመተባበር ብቻ ነው ብለዋል።

የክልሉ መንግስት ከውስጥም ከውጭም እየደረሱ ያሉ ጫናዎችን ለመቋቋም በሰከነ መንገድ ሥራዎችን እየሰራ መኾኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

“ሸኔ እና ትህነግ መጠነ ሰፊ ጥፋት እየፈፀሙብን ነው” ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።

ይህን መጠነ ሰፊ ጥቃትና ጥፋት የሚያቀናብሩትንና በክልሉ ውስጥም ከክልሉ ውጭም ባሉ አካባቢዎች እያደረሱት ያለውን የጥፋት አጀንዳ ለማክሸፍ ጠንካራ መንግስታዊ መዋቅር መፍጠር አስፈላጊ በመኾኑ የክልሉ መንግስት ይህንን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እየሠራን ነው ብለዋል።

በክልሉ ውስጥ ለአብነት ከሰሞኑ በአጣዬና አካባቢው የደረሰው ጥቃት በተደጋጋሚ ረፍት ለመንሳት የሽብር ቡድኖች የጠነሰሱልን ሴራ አካል ነው ብለዋል።

በተለያዩ አካባቢዎች በሚደርሱ ጥፋቶች ሁሉ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ ሀዘን እንደሚሰማው የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ የዚህ ሁሉ ችግር ማሰሪያው ሰከን ባለ መንገድ ስር የሰደዱ ችግሮችን ለመፍታት ተደማምጦ በመሥራት በመኾኑ ለዚህ ተግባራዊነት ሁሉም ሊረባረብ ይገባል ብለዋል።

በአማራ ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት የመጀመሪያ ተጎጅ አማራውን ያድርግ እንጅ የመላው ኢትዮጵያውያን ጥቃት መኾኑን በመገንዘብ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ እየደረሰ ያለውን ጥፋት በቃ ሊለው ይገባል ብለዋል።

የኅብረተሰቡ ተወካዮችም የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ላይ ይገኛሉ።

ዘጋቢ፦ ኤልያስ ፈጠነ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼

ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleMaxxansa Gaazexaa Hirkoo Waxabajjii 30/2014
Next article“የተደቀነብንን የደኅንነት ሰጋት መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት ሊፈታልን ይገባል” የሰሜን ሸዋ ዞን ነዋሪዎች