“ኢትዮጵያ የገጠሟት ፈተናዎችን ለመሻገር የጠነከረ የሕዝብ አንድነት እና መተባባር ያስፈልጋል” በሰሜን አሜሪካ ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ አባላት

317

ሐምሌ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ የገጠሟት ፈተናዎችን ለመሻገር የጠነከረ የሕዝብ አንድነት እና መተባባር እንደሚያስፈልግ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ አባላት ገለጹ።

በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው 39ኛው ዓመታዊ የስፖርት ፌስቲቫል ትናንት የኢትዮጵያ ቀን በሜሪላንድ ግዛት ተካሂዷል።

የዝግጅቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያያት ኢትዮጵያን እየፈተኗት ካሉት የንጹሐን ግድያ፣ መፈናቀል፣ እና ግጭት ወጥታ ወደምትታወቅበት ሰላም እና መረጋጋት እንደትመለስ በሕዝቡ ዘንድ አንድነት፣ ትብብር እና መተማመንን መጎልበት አለበት ብለዋል።

ዝግጅቱ በዳያስፖራው ዘንድ የበለጠ ቅርርብ እና በኢትዮጵያ ጉዳይ በአንድ እንዲቆሙ በማድረግ ረገድም የላቀ ሚና እንዳለውም አስተያየት ሰጭዎቹ ገልጸዋል። ይህን መሰል ዝግጅቶች በተለይ በአሜሪካ ተወልደው ላደጉ ወጣት ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከእናት ሀገራቸው ጋር ያላቸው ትስስር ለማጎልበት፣ የአትዮጵያን ባህል፣ ቋንቋ እና ሌሎች መስተጋብሮች እንዲያውቁ ለማስቻል ፋይዳው የጎላ እንደኾነም ነው የተገለጸው።

የዳያስፖራው መሰባሰብ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረጉ አላስፈላጊ ጫናዎችን በአንድነት ኾኖ ለመከላከል ብሎም ተሰሚነትን ለማሳደግ አስፈላጊ መኾኑንም ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል።

❝ኢትዮጵያውያን በረጅም ታሪካችን በርካታ ፈተናዎችን በአንድነት ቆመን መክተናል፤ አሁን የገጠሙንን ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመቅረፍም ከልዩነት ይልቅ በጋራ መቆም መተኪያ የሌለው አማራጭ ነው❞ ብለዋል አስተያየት ሰጪዎች።

በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ዐቢይ ኑርልኝ እንደገለጹት ዝግጅቱ ላለፉት 39 ዓመታት በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን የሚገናኙበት ጠንካራ የአንድነት መድረክ ኾኖ ቀጥሏል።

ከስፖርት ውድድሩ ጎን ለጎን አልባሳት፣ ቅርጻ ቅርጾች፣ ሥዕሎች፣ ባህላዊ ምግቦች፣ ቡና፣ ሙዚቃ እና ሌሎች የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋወቁ በርካታ ዝግትች ለዕይታ ቀርበዋል።

በአሜሪካ ሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ ዝግጅት 65 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ እትዮጵያን ከመላው የአሜሪካ ግዛቶች ብሎም ከሌሎች የዓለም ክፍሎች በመገኘት መታደማቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲን መረጃ ጠቅሶ ኢብኮ ዘግቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼

ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

Previous article“ለበይክ፡ የባሪያህን የኢብራሒምን ጥሪ ሰምተን መጥተናልና”
Next articleበኩር ጋዜጣ – ሐምሌ 04/2014 ዓ.ም ዕትም