
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሳውዲ አረቢያ አረፋ ተራራ ላይ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሙስሊም ምእመናን በፀሐይ መውጫ ላይ ተሰባስበው የአረፋ በዓልን እያከበሩ ነው።
በስፍራው የተገኙት የእምነቱ ተከታዮች በዓመታዊው የሐጅ ጉዞ ፍጻሜው የአላህን ይቅርታ፣ ሰላምና ምህረት ለማግኘት እጃቸውን ዘርግተው ተማጽነዋል።
ነጭ ካባ ለብሰው ነቢዩ መሐመድ የመጨረሻ ስብከታቸውን ያደረጉበትን የአረፋትን ሜዳ የሚቆጣጠረውን ዓለታማውን የምህረት ተራራ በመውጣት በዓሉን እያከበሩ መኾኑ ነው የተነገረው።
ብዙ በሐጅ ላይ ያልተገኙ ሙስሊሞች ይህንን ቀን በፆም እና በፈጣሪ ልመና ያሳልፋሉ።
ሀጃጆች ወደ ሙዝደሊፋ ሜዳ ከመሄዳቸው በፊት ጀንበር እስክትጠልቅ ድረስ ይቆያሉ። ጀማራት ተብሎ የሚጠራው የመጀመርያው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ወይም የመስዋዕትነት በዓል ሲሆን ይህም ቅዳሜ በመላው ዓለም በሚገኙ ሙስሊሞች ዘንድ የሚከበር መኾኑን ሲጅቲኤን ዘግቧል።
በምስጋናው ብርሃኔ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/