
ሐምሌ ዐ1/ 2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዐሻራ ያረፈበት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያለአንዳች የፀጥታ ችግር ግንባታው እየተከናወነ ይገኛል። ሠራዊቱ በቀጣናው አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን ግዳጁን ቀን ከሌት በማከናወን ላይ እንደሚገኝ በምዕራብ ዕዝ የሜካናይዝድ ሞተራይዝድ ብርጌድ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ንጋቱ አሰፋ ገልጸዋል።
ብርጌዱ በሕዳሴው ግድብ ሊቃጣ የሚችል ማንኛውንም አይነት ጥቃት ለመቀልበስ በሚያስችል ቁመና ላይ መኾኑን ተናግረዋል። ብርጌዱ ካሁን ቀደም በተሰለፈባቸው አወደ ውጊዎች አንፀባራቂ ገድል በመፈጸም ሕዝብ እና መንግሥት ያኮራ ተግባር መፈጸም መቻሉን አስታውሰዋል። በቀጣይም ጥንካሬውን ይዞ የሚቀጥልበትን አቅም ፈጥሯል ብለዋል።
የብርጌዱ ምክትል አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ሽፈራው ታያቸው በበኩላቸው ጠላት ቀጣናውን ለማተራመስ በቅጥረኛ ተላላኪ ኃይሎች አማካኝነት በተደጋጋሚ ትንኮሳ ቢሞክርም የሞተራይዝድ ብርጌዱ ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ ሰላም ማስፈን መቻሉን ገልጸዋል።
በቀጣናው የተሰማራው የሜካናይዝድ ብርጌድ ሊፈጠር ለሚችል የፀጥታ ስጋትን በአስተማማኝ ለመመከት በተጠንቀቅ ኾኖ ግዳጁን በመፈጸም ላይ እንደሚገኝም አዛዦቹ ማረጋገጣቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/