
አዲስ አበባ: ሐምሌ 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በወለጋ አካባቢ በአማራ ተወላጆች ላይ በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለዉን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ በዘላቂነት ማስቆም የሚቻለዉ የችግሩ ምንጭ የኾነዉን መዋቅር ማስተካከል ሲቻል እንደኾነ ጠበቃ እና የሕግ አማካሪዉ ነብዩ ምክሩ ገልጸዋል፡፡
በአካባቢዉ ያለዉ የጸጥታ እና ደኅንነት መዋቅር ችግሩን ቀድሞ ማነፍነፍ እና ማስቀረት አለመቻሉ ሊያስጠይቀዉ ይገባልም ብለዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ወለጋ በተለይም ደንቢ ደሎ፡ ጊንቢ እና ቄለም ወለጋ አካባቢዎች በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለዉ ዘርን መሰረት ያደረገ ጭፍጨፋ ከመደጋገሙ የተነሳ እንደተራ ወንጀል እየተቆጠረ መጥቷል ብለዋል፡፡
የዜጎች ደኅንነት በመንግሥት መዳፍ ስር በመኾኑ ደኅንነታቸዉን መጠበቅ ተቀዳሚ ተግባሩ እንደኾነ የሚናገሩት አቶ ነብዩ በአካባቢዉ ያለዉ የጸጥታ መዋቅር ችግሩን ቀድሞ ማነፍነፍ እና ማስቀረት አለመቻሉ ኀላፊነቱን የመወጣት አቅም እንዳነሰው ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ኅብረተሰቡን ያላሳተፈ የወንጀል መከላከል እና የጸጥታ ሥራ ዉጤታማ እንደማይኾን የሚናገሩት አቶ ነብዩ የጥቃቱ ሰለባዎች በጸጥታ መዋቅሩ ዉስጥ ተካተዉ የመፍትሄ አካል መኾን አለመቻላቸዉ እየተፈጠረ ያለዉን ችግር አክፍቶታል ይላሉ፡፡
የሰላም እንቅልፍ መተኛት ከፈለክ ለጎረቤትህ ደኅንነት ተጨነቅ ነዉና ነገሩ በወለጋ እየፈሰሰ ያለዉን የንጹኃን ደም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያወግዘዉ እና ዳግም እንዳይፈጸም ዘብ ሊኾን ይገባል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- በለጠ ታረቀኝ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/