‹‹አስተሳሰባችንን ሀገራዊ፣ እንቅስቃሴያችንን ደግሞ አካባቢያዊ በማድረግ ጽንፈኞችን መታገል ይገባል›› አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋየ

280

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋየ በአማራ ብሔር ላይ እየደረሰ ባለው ጭፍጨፋ ማዘናቸውን ገልጸዋል፤ ድርጊቱንም አውግዘዋል፡፡

አፈ ጉባኤዋ በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሱ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የክልሉ ምክር ቤት ከአጎራባች ክልሎች ምክር ቤቶች ጋር ውይይቶችና ምክክሮች መደረጋቸውን አንስተዋል፡፡

በአካባቢው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኹለንተናዊ እንቅስቃሴ ላይ ተሳታፊ መኾን የሚችሉበትን መንገድም ውይይቶች መደረጋቸውን ነው አፈ ጉባኤዋ የገለጹት፡፡

በዚህም ከቤንሻንጉልና ከአፋር ክልል ጋር መልካም ግንኙነት መፍጠር መቻሉን ለአብነት አንስተዋል፡፡

ከኦሮሚያ ክልል ጋርም በተመሳሳይ ተደጋጋሚ ውይይቶች ተደርገዋል፤ ተጠያቂነትን ለማስፈንም የኹለቱ ምክር ቤቶች በጋራ እየሠሩ እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡

ምክር ቤቶች መንግሥት የጀመረውን ሕግ የማስከበር ሥራ በመደገፍ ወንጀለኞችን ለሕግ የማቅረብ ሥራ እየሰሩ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት ጠላት ሀገርን ለማፍረስ ብሄርንና ሃይማኖትን እንደ አላማ ማሳኪያ ስራቴጅ አድርጎ ሲሠራ መቆየቱን ያነሱት አፈ ጉባኤዋ ይሕ ትውልድ በመደማመጥና በመቻቻል ሀገሩን ለመጭው ትውልድ የማስረከብ ታሪካዊ ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡ ይሕንን ለማድርግ ደግሞ ለአንድ ወገን ብቻ የሚተው ሳይኾን የመላው ሀገራችን ሕዝቦችንን ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል፡፡

‹‹ጽንፈኝነት መጨረሻው ጥፋት በመኾኑ አስተሳሰባችን ሀገራዊ፣ እንቅስቃሴያችን ደግሞ አካባቢያዊ በማድረግ ጽንፈኞችን መታገል ይገባል›› ብለዋል አፈ ጉባኤ ፋንቱ፡፡

ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼

ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየፊንላንድ መንግሥት ለአማራ ክልል የመልሶ ግንባታ የሚውል ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ።
Next articleኢትዮጵያ ለድህረ ግጭት ማገገሚያ የሚውል ወሳኝ የሚባል የፋይናንስ ድጋፍ እንዲደረግላት ጠየቀች።