የፊንላንድ መንግሥት ለአማራ ክልል የመልሶ ግንባታ የሚውል ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ።

136

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሚስ ኦውቲ ሆሎፓይነን ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
የፊንላንድ መንግሥት በአማራ ክልል በግብርና ልማት፤ በመጠጥ ውኃ፧ በመሬት አሥተዳደርና በትምህርት መስክ ላለፉት 10 ዓመታት ሰፋ ያለ እገዛና ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አንስተዋል።
አማራ ክልል በአሁኑ ወቅት መልሶ ለማቋቋምና ለመገንባት በሚያደርገው ጥረት የፊንላንድ መንግሥት አጋዥነቱን ለማሳየት 10 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።
አምባሳደሯም ድጋፉን ለርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) አስረክበዋል። ወደፊትም በተመረጡ የልማት ዘርፎች ላይ ድጋፉ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በከፈተው ጦርነት አማራ ክልል ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ለአምባሳደሯ ገልጸውላቸዋል።
የፊንላንድ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር የረጅም ዓመታት ወዳጅነት እንዳለው ያነሱት ርእሰ መሥተዳድሩ ለአማራ ክልል የመልሶ ግንባታ ላደረገው የገንዘብ ድጋፍ አመስግነዋል። በቀጣይ ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎችም አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።
የፊንላንድ መንግሥት ባለፉት 10 ዓመታት ከ50 ሚሊዮን ዩሮ በላይ በአማራ ክልል ለሚከናወኑ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ድጋፍ ማድረጉ ታውቋል።
ከ60 ዓመታት በላይ በዘለቀው የኢትዮጵያና ፊንላንድ ግንኙነት ፊንላንድ በግብርና፣ በትምህርት፣ በዴሞክራሲ ልማትና በሰብዓዊ መብት አያያዝ ለኢትዮጵያ ድጋፍ አድርጋለች፤ በሰብዓዊ ድጋፍም ትብብር ታደርጋለች።
ዘጋቢ፡- ስማቸው እሸቴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ሽብርተኞች ዓላማ እና ግብ የላቸውም፤ ተልዕኳቸው ኢትዮጵያን መፈተን ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article‹‹አስተሳሰባችንን ሀገራዊ፣ እንቅስቃሴያችንን ደግሞ አካባቢያዊ በማድረግ ጽንፈኞችን መታገል ይገባል›› አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋየ