“ሽብርተኞች ዓላማ እና ግብ የላቸውም፤ ተልዕኳቸው ኢትዮጵያን መፈተን ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

180

ሰኔ 30/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች 6ኛው ምክር ቤት በ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ጉባዔ በወቅታዊ ጉዳዮች ከምክር ቤት አባላቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በቀረቡ ጥያቄዎች ተጀምሯል፡፡ የምክር ቤት አባላቱ ወቅታዊ የሽብር ጭፍጨፋውን አስመልክቶ ማብራሪያ እንዲሰጧቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዓለም ታሪክ ከድንበሯ አልፋ አህጉራዊ የነጻነት ታሪክ ያላት ሀገር ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ባለው ጂኦ ፖለቲካዊ ምክንያቶች የዜጎቻችን ደኅንነት ፈተና ውስጥ ወድቋል ብለዋል፡፡

ሽብር ዓለም አቀፋዊ ፈተና ነው፤ ኢትዮጵያም በሽብርተኞች እየተፈተነች ነው ብለዋል፡፡

የሽብርተኞችን ጥቃት ለመከላከል እና ንጹሐንን ለመታደግ ሲሉ ሕይዎታቸውን መስዋእት ያደረጉ በርካታ የጸጥታ አባላት እንዳሉም አውስተዋል፡፡

ንጹሐንን የጨፈጨፉ ሽብርተኞች በየትኛውም መንገድ ሲለካ ምክንያታዊ አይደሉም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጊዜ ይወስዳሉ፤ ዋጋ ያስከፍሉናል እንጂ ከሕግ አያመልጡም ብለዋል፡፡

“ሽብርተኞች ዓላማ እና ግብ የላቸውም፤ ተልዕኳቸው ኢትዮጵያን መፈተን ነው” ብለዋል፡፡

ሽብርተኞቹ ዓላማቸው እግር እና ጭንቅላት የኾኑላቸውን ኅይሎች ተልዕኮ ማስፈጸም በመኾኑ ድርጊታቸው ውስብስብ እና አድካሚ መኾኑ ግምት ውስጥ ሊገባ ይገባል ብለዋል፡፡

መንግሥት የመረጠውን ሕዝብ ደኅንነት የማስጠበቅ ኅላፊነት እንዳለበት በምክር ቤቱ አባላት ተነስቷል፤ ጥያቄውም ትክክል እና ተገቢ መኾኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሕዝብም የመረጠውን መንግሥት ማድመጥ እና በጋራ ቆሞ መከላከል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

ሽብርተኞቹ ኢትዮጵያን ለመበተን የሚሹ አካላትን ፍላጎት እንደሚያስፈጽሙ በገሃድ ያመላከተ ድርጊት እየተፈጸመ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የንጹሐንን ሕይዎት ለማትረፍ እና ሀገርን ለመታደግ ጠያቂ ብቻ ሳይኾን ኀላፊነት የሚሰማቸው እና ኀላፊነታቸውን የሚወጡ ዜጎች ያስፈልጋሉ ብለዋል፡፡

የሽብር ተግባራት አሁንም ድረስ በተለያየ መንገድ እየተቀነባበሩ በመኾኑ በጋራ ለመከላከል የጸጥታ እና የደኅንነት አካላትን ማገዝ ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼

ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠየቀ።
Next articleየፊንላንድ መንግሥት ለአማራ ክልል የመልሶ ግንባታ የሚውል ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ።