“በንጹሓን ላይ የሚደረገው ጭፍጨፋ ዳግም እንዳይፈጠር ቅድመ ጥንቃቄ እና ጥበቃ ማድረግ በየደረጃው ያለ የመንግስት ግዴታ በመኾኑ ኀላፊነት ሊወስድ ይገባል።” በኢትዮጵያ የስነ መለኮት ድህረ ምረቃ ት/ቤት አካዳሚክ ዲን ልደቱ ዓለሙ (ዶ/ር )

197

አዲስ አበባ፡ ሰኔ 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በንጹሀን ላይ የሚደረገው ጭፍጨፋ ዳግም እንዳይፈጠር ቅድመ ጥንቃቄ እና ጥበቃ ማድረግ በየደረጃው ያለ የመንግስት ግዴታ በመኾኑ ህጋዊ እና ህሊናዊ ኃላፊነትን መውሰድ አለበት ሲሉ በኢትዮጵያ የስነ መለኮት ድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት አካዳሚክ ዲን ልደቱ ዓለሙ አሳሰቡ።
በወለጋ አካባቢ በአማራዎች ላይ የተፈጸመዉ ጭፍጨፋ ኹሉንም ኢትዮጵያዊ ሊያመዉ እና ድርጊቱን በጥብቅ ሊያወግዘዉ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
ሰዉ ሆነዉ የሰዉነትን ክብር ዝቅ ያደረጉ እና ያረከሱ፤ ሰዋዊ ፍላጎታቸዉን እዉን ለማድረግ የሰዉን ህይዎት ማጥፋት ምንም የማይመስላቸዉ ፤ ሰዉነትን ያልተላበሱ አረመኔዎች ነፍስ ያላወቁ ህጻናትን፣ አረጋዊያንን እና እናቶችን ህይዎት በሰቃቂ ሁኔታ ነጥቀዋል፡፡
እንዲህ አይነት አረመኔያዊ ጭፍጨፋዎች ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ አካባቢ በሚኖሩ አማራዎች ላይ ሲደጋገም መጥቷል፡፡
ሀገር በመሪዎች እጅ ነች፣ መሪ ሲባል ደግሞ በመንግስት መዋቅር ስር ብቻ ያሉት አይደሉም ፤ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ የማህበረሰብ አንቂዎች እና ተዕጽኖ ፈጣሪዎች ጭምር እንጅ። የሚፈጠረዉ ችግር ከእነዚህ አካላት በላይ ሆኖ አይደለም፤ የነገን ሀገራዊ አደጋ ታሳቢ በማድረግ ቆም ብሎ ማሰቡ እና ችግሩን ማድረቁ ይሻላል ይላሉ ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት በኢትዮጵያ የስነ መለኮት ድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት አካዳሚክ ዲን እና የተቋሙ ድርጅታዊ አመራር መምህር ልደቱ ዓለሙ (ዶ/ር) ።
እንዲህ ዓይነት ችግሮች በተመሳሳይ አካባቢዎች መደጋገማቸዉን የሚናገሩት ዶ/ር ልደቱ ፤ ጥቃት ፈጻሚዎችን እና አስፈጻሚዎችን መለየት ብቻም ሳይኾን ለምን እንደሚፈጽሙ መመርመር ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ቁልፍ መንገድ ነዉ ይላሉ፡፡
ብልህ ከትናንት ይማራል እንዲሉ ያለጊዜያቸዉ ለባከኑ ነፍሶች ፍትህ ከማሰጠትም ባሻገር ነገ ደግሞ በሌሎች ንጹሓን ላይ ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር ቅድመ ጥንቃቄ እና ጥበቃ ማድረግ የመንግስት እና በመሪነት የሚመደቡ የማህበረሰብ ክፍሎች ሊወጡት የሚገባ ህጋዊ እና ህሊናዊ ኃላፊነታቸዉ ሊሆን ይገባል ብለዋል ዶ/ር ልደቱ፡፡
ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዊያን ስሪት ናት፤ የአንዱ መጉደል የሚያጎድለዉ ኢተዮጵያን በመኾኑ የአንዳችን ህመም ሌላችን ሊያመን እና ችግሩን በጋራ ከማዉገዝም ባሻገር እርስ በእርሳቸን ጠበቃዎች ልንኾን ይገባልም ብለዋል፡፡
ዘጋቢ ፦ በለጠ ታረቀኝ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleʺየሞቱት ያስለቅሳሉ፣ የተረፉት ያስጨንቃሉ”
Next articleየአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠየቀ።