
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል መንግስት በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ውስጥ በሚኖሩ ንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።
የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በሰጡት መግለጫ፣ አሸባሪው የሸኔ ቡድን ዛሬም ሰላምን በሚሻው ንጹሃን ሕዝባችን ላይ የሞት ጽዋን የሚያዘንብ የጥፋት መልአክ ኾኗል ብለዋል።
ከማንኛውም የሰው ዘር ጋር በሰላም መኖርን፣ ሠርቶ መበልጸግንና አግኝቶ መደሰትን ብቻ የሚሻው የአማራ ሕዝብም ሆነ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ወገኖች ሰላምን በማይሹ የሀገርና የሕዝብ ጠላቶች እንዲህ የመጠቃታቸው ብቸኛው ግብ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማንበርከክ አልመው መሆኑን ገልጸዋል።
በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ውስጥ በሚኖሩ ንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ ለመላው ሕዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል።
ዛሬም ሆነ ነገ የዚህ ችግር ብቸኛው መፍትሔ የሕዝባዊ አንድነት ጠላት እና በጋራ ሠርቶ የማደግ ደመኛ የሆኑ ፀረ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የሆኑ ሁሉንም ኃይላት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንደ ሕዝብ በአንድነት ታግሎ ማሸነፍ ሲቻል ብቻ መሆኑን አመላክተዋል።
ይህን መሰል ጥቃቶችን በመፈጸም መሪር ሀዘን ላይ የሚጥሉንን ጠላቶቻችንን ታግሎ ለማሸነፍና ለዚህ ጉዳይ ከሥሩ መፍትሔ ለመፈለግ ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድ ድምጽ ይህን ድርጊት በመቃወም የመፍትሔው አካል ሊሆን ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/