ለሀገራዊ ምክክር የተመረጡ ኮሚሽነሮች ለሀገራቸው መልካም በመሥራት ባለውለታነታቸውን እንዲያተርፉበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ጠየቁ።

133

አዲስ አበባ: ሰኔ 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከተመረጡ 11 ኮሚሽነሮች ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ተወያይተዋል።

ለሀገራዊ ምክክር መድረክ ስኬታማነት መንግሥት የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

ለሀገራዊ ምክክር መድረክ የተመረጡ ኮሚሽነሮች ለሀገራቸው መልካም በመሥራት ባለውለታነትን የሚያተርፉበት በመኾኑ አጋጣሚዉን በአግባቡ እንዲጠቀሙበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ጠይቀዋል።

ኮሚሽኑ የአራት ወራት ተግባራቱን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረበ ሲኾን የሚመራባቸውን ሕግና ደንቦች ማውጣት፣ በአምስት ክልሎች እና አንድ ከተማ አሥተዳደር ስለ ሀገራዊ ምክክሩ አስፈላጊነት የሚመለከታቸውን ባለ ድርሻ አካላት አግኝቶ ማነጋገሩን እና ጥሩ ግብዓት ማግኘት መቻሉንም ተናግረዋል።

ከዓለምአቀፍ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በመወያየት ግብዓቶች መገኘታቸውን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ተናግረዋል።

በክልል እና ዞኖች ቢሮዎች ን መክፈት እና የተለያዩ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በቀጣይ እንደሚከናወኑም ተገልጿል።

ዘጋቢ:- በለጠ ታረቀኝ -ከአዲስ አበባ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼

ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከ10 ሺህ ኩንታል በላይ የምግብ እህል ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ፡፡
Next article❝አሸባሪውን የሸኔ ቡድን እስከመጨረሻው ተከታትለን ከሕዝባችን ጋር እናስወግደዋለን❞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)