
ጎንደር: ሰኔ 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ባሉ ወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች የተሰበሰበ ከ10 ሺህ ኩንታል በላይ የምግብ እህል በክልሉ ጉዳት ለደረሰባቸው ዞኖች እንዲከፋፈል ለአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ እና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስረክቧል።
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ወርቁ ኃይለማርያም እንደገለጹት ድጋፉ በመጠለያ ጣቢያ ለተጠለሉ ወገኖች የሚደርስ ይኾናል ብለዋል።
ተጎጅ ወገኖች ወደመደበኛ ሕይወታቸው እስኪመለሱ ድረስ ዞኑ የተቻለውን ኹሉ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጃለም ለተፈናቀሉ ወገኖች እየተደረገ ያለው ድጋፍ አናሳ መኾኑን ገልጸዋል፡፡
ከረጅ ድርጅቶችና ከመንግሥት ድጋፍ ለማሰባሰብ ጥረት ቢደረግም በተፈለገው ልክ ማግኘት አልተቻለም ብለዋል፡፡ በዚህም ምክንያት አሁን ላይ 11 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሕዝብ ለከፍተኛ የምግብ ችግር መጋለጡን ገልጸዋል፡፡
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ያደረገው ድጋፍ ያለውን የምግብ እጥረት በመጠኑ ያስታግሳል ነው ያሉት ኮሚሽነር ዘላለም፡፡ ይህን አርዓያነት ያለው ተግባር ሌሎች አካባቢዎችም ሊተገብሩትና ለወገን ሊደርሱ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡- መሠረት ባዬ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/