
ደብረ ብርሃን: ሰኔ 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የ2014 የበጎ ፈቃድ አረንጓዴ ዐሻራ መርኃግብር ማስጀመሪያ ከኹሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በተወጣጡ ወጣቶች በደብረብርሃን ከተማ እየተከናወነ ነው።
ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡ ወጣቶች በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ መልዕክት የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃግብር እየተከናወነ ነው።
ኢትዮጵያ በበርካታ መሰናክሎች ውስጥ እንደመገኘቷ መጠን ወጣቶች ሀገርን የማስቀጠል ኀላፊነታችሁን ልትወጡ ይገባል ሲሉ የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ካሳሁን እምቢዓለ ለወጣቶቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ኢትዮጵያዊነት ማንም ሲያሻው የሚነጥቀን ሲያሻው የሚቸረን ባለመኾኑ ሀገርን አፅንቶ በማቆም በኩል ወጣቶች የጎላ ሚና አላቸው ነው ያሉት።
ወጣቶቹ ከሚያከናውኑት የችግኝ ተከላ መርኃግብር ጎን ለጎን የአረንጓዴ ዐሻራ ተግባር የአየር ንብረት ለውጥ ሚዛንን መጠበቅ ስላለው ኹለንተናዊ ፋይዳ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት አድርገዋል።
ከኹሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተወጣጡት ወጣቶቹ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራቸው በተለያዩ ቦታዎች የችግኝ ተከላ ሥራ፣ የደም ልገሳ ሲያከናውኑ የከተማ ግብርና ሞዴል ሥራዎችን መጎበኘት አንዱ የመርኃግብሩ አካል ነው ተብሏል።
በመርኃግብሩ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተዋል።
ዘጋቢ:- ኤልያስ ፈጠነ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/