
ሰኔ 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል በዕዙ ሥር ከሚገኙ የሠራዊቱ ክፍሎች የተወጣጡ የዘመቻ ሙያተኞችን አሰልጥኖ አስመርቋል።
በማዕከሉ ሲሰጥ በቆየው ሙያዊ ሥልጠና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂዎች የተዘጋጀላቸውን ሽልማት የማሰልጠኛ ማዕከሉ ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሎኔል ሁሴን አስረስ አበርክተዋል።
ኮሎኔል ሁሴን እንዳሉት ዕዙ የሚሰጠውን ማንኛውም ተልእኮ በድል ለመወጣትና የሠራዊቱን የውጊያ ዝግጁነት ከምንጊዜውም በበለጠ ለማረጋገጥ የዘመቻ አመራር እና ሙያተኞች በዘርፉ ዕውቀት ላይ የተመሰረተ ክህሎት ሊኖራቸው ይገባል።
ተመራቂ የዘመቻ ሙያተኞች የሠራዊቱን የውጊያ ዝግጁነት በማሳደግ የዕዙን ግዳጅ አፈጻጸም ውጤት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችላቸውን ሙያዊ ክህሎት መገንባታቸውን ገልጸዋል።
የሠራዊቱን ሞራላዊና ሥነልቦናዊ ዝግጁነቱን መገንባት የሙያተኞቹ ቀዳሚ ተግባር ሊኾን ይገባል ያሉት ኮሎኔሉ በሥልጠናው የቀሰሙትን ዕውቀት ተጠቅመው ሠራዊቱ በውጊያ ሳይንስ እና ጥበብ ላይ የተመሰረተ ክህሎት እንዲኖረው ማብቃት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
ተመራቂ ሙያተኞች በሰጡት አስተያየት በማሰልጠኛ ማዕከሉ የቀሰሙትን ክህሎት በመጠቀም የሠራዊቱን የውጊያ አቅም የበለጠ ለማሳደግ እንደሚሠሩ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/