
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አባላቱ የሀገርን ዳር ድንበር ከዉጭ ወራሪ ኀይልና ከውስጥ ፀረ ሰላም ኀሎች ለመከላከል እና የሚሰጣቸውን ግዳጅ በድል ለበወጣት ሌት ተቀን ዝግጁነት የማረጋገጥ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
በክፍለ ጦሩ የሚገኘው የ2ኛ ሬጅመንት አዛዥ ሻለቃ አለምነው ተፈራ እንደተናገሩት ሰራዊቱ ተልዕኮውን እና አላማዉን በሚገባ የሚያዉቅ፣ በወታደራዊ ድሲፒሊን የተገነባ ስለሆነ ማንኛውንም ግዳጅ የሚፈፅመው አሰራሩን እና ደንቡን በመከተል ነው፡፡
የሻለቃው አዛዥ አክለውም ሠራዊቱ ወታደራዊ ሳይንስና ጥበብን በሚገባ እንዲላበስ በስልጠና በማብቃት የሀገሩን ሉአላዊነት ክብር በመስዋትነቱ የሚያስከብር አመራርና አባላት ፈጥረናል ብለዋል፡፡
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመድፈር የሚመጣ ጠላት እና ሰላማችንን ለማወክ የሚሯሯጡ የውስጥ ፀረ ሰላም ሃይሎችንም ይሁን ተላላኪ ባንዳዎች ለመደምሰስ ሰራዊቱ ከምንግዜውም በላይ በአስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ሻለቃ አለምነው ተፈራ ተናግረዋል፡፡
በሜካናይዝድ ክፍለ ጦር የአየር መቋዋሚያ ምክትል አዛዥ ሻለቃ መኳንት ደርብ በበኩላቸው ሰራዊቱ ግዳጁን በአጭር ጊዜ እና በአነስተኛ ኪሳራ እንዲፈፅም የተቀናጀ የሜካናይዝድ ተኩስ ድጋፍ መስጠት የሚያስችል ስልጠና መሰጠቱንም ገልፀዋል።
የሜካናይዝድ አባላቱ ከእግረኛ ክፍለ ጦር ጋር በመቀናጀት የሀገር ሉአላዊነት እንዳይደፈር ሌት ተቀን ዝናብና ብርዱ ሳይበግራቸው የግዳጅ ቀጠናቸውን እየጠበቁ እንደሚገኙ ሻለቃ መኳንት ደርብ ተናገረዋል፡፡
እንደ መከላከያ ሰራዊት መረጃ ከሰራዊት አባላት መካከል ሃምሳ አለቃ ሲሳይ አበራ እና ምክትከል አስር አለቃ አቦነሽ ከበደ በሰጡት አስተያት ጀግኖች ደማቸውን ሰጥተው ያስከበሯትን እናት ሃገር በእኛ መስዋትነት ተከብራ እንድትቀጥል በማንኛወም ጊዜ የሚሰጣቸውን ግዳጅ በድል ለመወጣት ዝግጁ ነን ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/