ክልሎች ከድጎማ በጀትና ከጋራ ገቢዎች የሚያገኙት የገቢ ድርሻ እየጨመረ የመጣ ቢሆንም በክልሎች መካከል የሚታየው የዕድገት አለመመጣጠን እየጠበበ ባለመሆኑ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት እንደሚገባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስገነዘበ።

129

ባሕር ዳር: ሰኔ 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት በበይነ መንግሥታት የፊስካል ግንኙነቶች ላይ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ አመራሮችና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።

በመድርኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ክልሎች ከድጎማ በጀትና ከጋራ ገቢዎች የሚያገኙት የገቢ ድርሻ እየጨመረ የመጣ ቢሆንም በክልሎች መካከል የሚታየው የዕድገት አለመመጣጠን እየጠበበ ባለመሆኑ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

አፈ ጉባኤው አያይዘውም የፌዴራል ተቋማት ወደ ክልሎች የሚተላለፉ ውስን ዓላማ ያላቸው በጀቶች እና የፌዴራል መሠረተ ልማት ዝርጋታ በአሠራራቸውም ሆነ በስርጭታቸው ፍትሐዊነት ላይ ተደጋጋሚ ጥያቄ ሲነሳባቸው የቆየ በመሆኑ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌዴራል ተቋማት ግልፅ፣ አሳታፊና ተጠያቂነት ያለው አሠራር መዘርጋት አለባቸው ብለዋል።

በሚሠሯቸው ሥራዎች ፍትሐዊነትንና ውጤታማነትን እንዲያረጋግጡና ክትትልና ድጋፍ የማድረግ ኃላፊነት የተጣለባቸው ተቋማትም የተዘረጉት አሠራሮች በትክክል ተግባራዊ ስለመደረጋቸው ማረጋገጥ ያስችላቸው ዘንድ ደንብ ሊዘጋጅለት ይገባል ብለዋል፡፡

ከተለያዩ ሀገራት የተገኙትን ተሞክሮዎች መሠረት በማድረግ በሀገራችን ፍትሐዊና ውጤታማ የበይነ መንግሥታት ፊስካል ግንኙነቶችን ለማሳለጥ የሚያግዝ ሙያዊ ነፃነትና ብቃት ያለው ጠንካራ ተቋም ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት እውን ለማድረግ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ድጋፍ ያስፈልጋል ብለዋል አፈ ጉባኤው።

ፌዴሬሽን ምክር ቤት በሀገራችን ግልጽ፤ ፍትሐዊና ውጤታማ የፊስካል ሽግግር ሥርዓቶች እንዲዘረጉ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኝ ቢሆንም በምክር ቤቱ ጥረት ብቻ ፍትሐዊና ውጤታማ የፊስካል ሽግግር ሥርዓት ማረጋገጥ ስለማይቻል ሁለቱ ምክር ቤቶች በተቀናጀ መንገድ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡ ዘገባው የኢፕድ ነው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleአሸባሪው ትህነግ ሕዝብ እየሰበሰበ ለዳግም ጦርነት እየተዘጋጀ በመሆኑ ቡድኑን ለማሳፈርና ለማንበርከክ በተጠንቀቅ መጠበቅ እንደሚገባ የአማራ ክልል ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት አስገነዘበ።
Next articleጀግኖች ደማቸውን ሰጥተው ያስከበሯትን ሀገር በመስዋዕትነታችን እናስቀጥላለን ሲሉ በሰሜን ምዕራብ ዕዝ የሚገኙ ሜካናይዝድ እና የእግረኛ ክፍለ ጦር የሰራዊት አባላት ተናገሩ፡፡