
ባሕር ዳር: ሰኔ 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ኀላፊ አቶ ተፈሪ ታረቀኝ እንደገለጹት እንደ ሀገር አምራች ኢንዱስትሪው ላይ ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡ የኃይል አቅርቦት፣ ውጭ ምንዛሬ፣ የጥሬ እቃ ፣ የፋይናስ ችግሮች ዘርፉን እየፈተኑት እንደኾነም ጠቅሰዋል።
በተለይም በአማራ ክልል የኃይል አቅርቦት ችግር ኢንዱስትሪዎች በአቅማቸው ልክ እንዲሠሩ ማስቻል ቀርቶ አዳዲስ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ሥራ ለማስጀመርም የማይቻል አድርጎታል ነው ያሉት።
ክልሉ እንደ ሀገር ካለው የኃይል አቅርቦት ፍትሐዊ የኃይል ተጠቃሚ እንዲኾንም ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል። አምራች ኢንዱስትሪው ከውጭ ከሚያስገባቸው ማሽኖች በተጨማሪ ጥሬ እቃውንም ከውጭ ማምጣት አምራችነትን የሚፈትን ኾኗል ነው ያሉት ምክትል ቢሮ ኀላፊው።
አቶ ተፈሪ እንደተናገሩት የኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚመራበት ሥርዓት በራሱ ችግር ነበረበት። ተመጋጋቢ ኢንዱስትሪዎችን ታሳቢ አድርጎ የማስጀመር ችግር መኖሩንም ጠቅሰዋል። አንዱ ኢንዱስትሪ የሚያመርተው ለሌላው ኢንዱስትሪ ግብዓት መኾን ሲገባው፣ ሁሉም ግብዓቱን ከውጭ የሚያስገባበት ሁኔታ ችግሩን ተራዛሚ አድርጎታል ብለዋል።
ኢንዱስትሪውን ከግብርናው ዘርፍ ጋር በማስተሳሰር ለኢንዱስትሪ መጋቢ በማድረግ በኩልም ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን ምክትል ቢሮ ኀላፊው ገልጸዋል።
ምክትል ቢሮ ኀላፊው እሄን ያሉት ለሀገር አቀፍ የኢንተርፕራይዞች ልማት ዘርፍ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና በባሕር ዳር ከተማ እየተሰጠ ባለበት መድረክ ነው። በዘርፉ ላይ የተደቀኑ ተግዳሮቶችን እየፈቱ የባለሙያውን አቅም መገንባትም ሌላው አቅጣጫ ተደርጎ እየተሠራ እንደሆነ ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ጋሻው አደመ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/