
ባሕር ዳር: ሰኔ 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሚሊሻው የአስተሳሰብ አንድነት በመፍጠር ተልእኮውን በአግባቡ መፈፀም እንደሚገባው የአማራ ክልል ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ባምላኩ ዓባይ አሳስበዋል።
የአማራ ክልል ሚሊሻ ያካሄደውን የግዳጅ አፈፃፀምና የቀጣይ የግዳጅ ተልእኮ ዝግጅት በተመለከተ ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ የሚሊሻ መሪዎች በባሕርዳር እየመከሩ ነው። ምክክሩ አንድ የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር ለቀጣይ ለሚኖር ተልዕኮ ለመዘጋጀት እና ተልዕኮን በአግባቡ ለመወጣት ያለመ ነው።
ምክክሩን የመሩት የአማራ ክልል የሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ባምላኩ ዓባይ ሚሊሻው የአስተሳሰብ አንድነት በመፍጠር ለተልዕኮ ዝግጁ መሆን አለበት ብለዋል። ሚሊሻው በሕልውና ዘመቻው ከፈተኛ አስተዋጽኦ እንደነበረውም ገልፀዋል።
ሚሊሻው በግንባር በመዝመት ጠላትን ማሳፈር መቻሉንም አስታውቀዋል። የፀጥታው ዘርፍ በመርህና በብቃት መመራት መቻል አለበትም ነው ያሉት። ሚሊሻውን በተገቢው መንገድ መምራት የማይችል መሪ ከኃላፊነት መልቀቅ እና ተጠያቂ መሆን እንደሚገባውም ተናግረዋል። ከፍተኛ የሰው ኃይል ያለበትን የሚሊሻ ዘርፍ በተገቢው መንገድ ማብቃትና ማዘጋጀት ይገባልም ብለዋል።
ለሕዝብ ክብር የሚመጥን የሚሊሻ መሪ ሊኖር እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት። ሚሊሻው በከፍተኛ ቁርጠኝነት ለሕዝብ ክብርና ሕልውና መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ጀግኖቻችን እያደነቅን፣ ያልሰሩትን እየወቀስን ለተልዕኮ መዘጋጀት መቻል አለብንም ነው ያሉት። በአንድነት እንጂ በመከፋፈል የሕዝብን ደኅንነት እና ክብር ማስጠበቅ እንደማይቻልም ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/