“የሀገሪቱ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳይ አሁንም የመንግስት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ ነው!!” ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

292

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሀገሪቱ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳይ አሁንም የመንግሥት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ ሆኖ መቀጠሉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ ቤልለኔ ስዩም ገልፀዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይን በተመለከተ ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኀን መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫው በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በንጹሐን ዜጎች ላይ በአሸባሪዎች የተከሰቱት አሰቃቂ ግድያዎች ዜጎችን በመንግሥት ላይ ለማነሳሳት እና ለማስቆጣት ሆነ ተብሎ የተቀነባበሩ ድርጊቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የጠላት ኃይሎች በተቀናጀ መልኩ በሀገሪቱ አለመረጋጋት በመፍጠር ኢትዮጵያን ለመበተን እየሰሩ በመሆኑ መንግስት የሀገሪቱን ሰላም እና ደኅንነት በማረጋገጥ በያዘው የብልፅግና መንገድ ለመቀጠል ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ፕሬስ ሴክሬታሪዋ ገልፀዋል።
በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተሽከርካሪ እና በአየር ትራንስፖርት የሚደረገው የሰብዓዊ እርዳታ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ወይዘሪት ቢልለኔ ገልፀዋል።
4ኛው የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራምን በተመለከተም ዘንድሮ በሚኖረው ዘመቻ የሚተከሉ ችግኞች የአየር ንብረት ለውጥን ከመቋቋም ባለፈ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጥቅም በሚያስገኙ የአትክልት እና ፍራፍሬ ዝርያዎች ላይ ትኩረት ስለመደረጉ አብራርተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የቤት ሠራተኝነት የሞራልም የሕግም ማዕቀፍ ሊኖረው ይገባል” የቤት ሠራተኞች
Next articleበባሕር ዳር ከተማ የባጃጅ ወይም የባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እስከ ምሽቱ 2:00 ብቻ እንዲኾን ተገደበ፡፡