“የቤት ሠራተኝነት የሞራልም የሕግም ማዕቀፍ ሊኖረው ይገባል” የቤት ሠራተኞች

156

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የቤት ሠራተኞቹ መንግሥት የዓለም አቀፉን የሥራ ድርጅት ስምምነት 189/2003 ዓ.ም ተግባራዊ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን ዓለማቀፉን የቤት ሠራተኞች ቀንን አስመልክቶ ከአጋር አካላት ጋር የመወያያ መድረክ አዘጋጅቷል። መድረኩ የዓለም የቤት ሠራተኞች ቀንን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ እና የቤት ሠራተኞች ልክ እንደማንኛውም ተቀጣሪ መብቶቻቸውን የሚጠይቁበት እና ግዴታቸውን ሊወጡ የሚችሉበት የሕግ ማዕቀፍ ያስፈልጋቸዋል የሚል ዓላማን ያነገበ ነው።
የዓለም የሥራ ድርጅት የቤት ሠራተኞችም ጭምር ምቹ የሥራ ሁኔታ እንዲፈጠርላቸው ይደነግጋል።
በተጨማሪም ከማንኛውም ግዳጅና ተጽእኖ ነጻ የመኾን፣ከሕጻናት መብትና ጉልበት ብዝበዛ ነጻ የመኾን፣ ከአሠሪዎቻቸው ጋር ሕጋዊ የሥራ ውል እንዲኖር የመፈራረም እና መሰል መብቶች እንዲኖራቸውም ይደነግጋል።
በባሕር ዳር ተምሳሌት የቤት ሠራተኞች ማኅበር ሰብሳቢዋ ባንች ተፈራ የቤት ሠራተኝነት አማራጭ የሥራ መስክ እንጂ አማራጭ ስናጣ የምንሠራው ሥራ መኾን የለበትም ብላለች።
ለአሠሪውም ለሠራተኛውም የሚስማማው የዓለም የሥራ ድርጅት ድንጋጌ በሀገራችን ሊተገበር ይገባል ብላለች። ተምሳሌት የቤት ሠራተኞች ማኅበር የቤት ሠራተኞች መብቶቻቸው እንዲከበሩ፣ በሕገወጥ ደላሎች በደል እንዳይደርስባቸው ፣ለስደትና እንግልት እንዳይዳረጉ ፣የአሠሪዎችና ሠራተኞች መብትና ግዴታ እንዲታወቅና እንዲተገበር የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ እየሠራ መኾኑንም ሰብሳቢዋ ገልጻለች።
አሠሪም የሚያማርርበት፣ ሠራተኞችም ላልተገባ እንግልትና የመድልኦ ተጋላጭ የሚኾኑበት አሠራር መኖር የለበትም ሲሉ በመድረኩ የታደሙ የማኅበሩ አባላት ተናግረዋል።
ገና በአስር ዓመት እድሜዋ የቤት ሠራተኝነትን እንደጀመረች የተናገረችው መቅደስ አዘነ የቤት ሠራተኞች በአሠሪዎቻቸው የሚደርስባቸው አድሎዊነትና ብዝበዛ እነዲቆም የሕግ መዓቀፍ እንዲኖረው እጠይቃለሁ ነው ያለችው።
የቤት ሠራተኞች የሙያ ጉድለትና የብቃት ማነስ በግንዛቤና በመረዳዳት የሚቀረፍ መኾን አለበት ባይ ናት፡፡ መቅደስ በተለያዩ አደረጃጀቶች የሙያ ብቃታቸው ማሳደግ ይገባል ትላለለች፤ ተምሳሌት የቤት ሠራተኞች ማኅበርን እንደምሳሌ በመጥቀስ።
መቅደስ “የቤት ሠራተኝነት የሞራልም የሕግም ማዕቀፍ ሊኖረው ይገባል” ስትል ጠይቃለች፡፡
በመድረኩ ተገኙት የትዛዙ ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ኀላፊ አቶ ትዛዙ ደጀኔ የቤት ሠራተኞች መብት መከበር ሕግ ማዕቀፍ መኖር እንዳለበት ነው የጠቀሱት፡፡
በኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን የሴቶች ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ ራሄል አየለ የቤት ሠራተኞች ተገቢ ክፍያ፣ምቹ የሥራ ሁኔታ መጠበቅ አለበት ብለዋል፡፡ እንደ መንግሥት የሕጉ መጽደቅ ለሠራተኞች ምቹ የሥራ ሁኔታ ለአሠሪዎችም ሕግን መሰረት አድርጎ የመዋዋል መብትን ይሰጣል ሲሉ ገልጸዋል።
ከሕጉም በላይ አሠሪዎችም ኾኑ ማኅበረሰቡ የሕሊና እና የሞራል ተጠያቂነትን በማስቀደም ኀላፊነትን መውሰድ እንደሚገባ ወይዘሮ ራሄል ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ስለ የቤት ሠራተኞች መብትና ግዴታ የሚደነግገውን የዓለም የሠራተኞች ድርጅት አዋጅ 189/2003 ዓ.ም ተግባራዊ ለማድረግ መመሪያዎችና ደንቦች እንዲወጡ ጅምር ሥራ መኖሩን ጠቁመዋል፡፡ ሠራተኛ ማኅበራት፣ ኅብረተሰቡ፣የሕግ አካላት፣ የአሠሪና ሠራተኛ አገናኝ ድርጅቶች በአግባቡ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡
የዓለም የቤት ሠራተኞች ቀን ዘንድሮ በዓለም ለ11ኛ ፤ በኢትዮጵያ ለአራተኛ ጊዜ ተከብሯል።
ዘጋቢ:-ጋሻው አደመ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ለዓባይ ውኃ ጠብታ ውኃ የማታበረክተው ግብጽ በወንዙ ላይ መቶ በመቶ የመወሰን መብት መጠየቅ አትችልም” በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀድሞው የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዥ
Next article“የሀገሪቱ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳይ አሁንም የመንግስት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ ነው!!” ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት