
ፍኖተ ሰላም፡ ሰኔ 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የዱር ቤቴ – ቁንዝላ – ሻሁራ የመንገድ ፕሮጀክት 135 ኪሎ ሚትሮችን የሚሸፍን ኮንክሪት የአስፓልት መንገድ ነው።
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የሚያስገነባው ይህ የመንገድ ፕሮጀክት ከ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ተበጅቶለታል።
በዲዛይንም በግንባታም የመንገድ ሥራውን የቻይናው ዜድ ሲሲሲ (ZCCC) ዓለም አቀፍ ሥራ ተቋራጭ ድርጅት ውል ወስዶ እየሠራ ነው።
ተቋራጩ መንገዱን ሰርቶ ለማጠናቀቅ የሶስት ዓመት ውል የወሰደ ሲኾን ነሐሴ 6/2013 ዓ.ም ነበር ሥራውን በይፋ የጀመረው።
የፕሮጀክቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ባይ ያን ዌይ (ኢንጅነር ) እንደተናገሩት የመጀመሪያው ስድስት ወራት በዲዛይን ሥራና ለሥራው የሚያስፈልጉ መሰረታዊ እቃወችን በማጓጓዝ፣ የካምፕ ሥራ እና የመሳሰሉ ጉዳዮችን በፈጸም አሳልፏል ብለዋል። አሁን ላይ ጠቅላላ የመንግድ ግንባታው ሶስት በመቶ መድረሱንም አስረድተዋል።
አሁን ላይ ደግሞ ወደ ዋናው የመንገድ ግንባታ ሥራ ተገብቷል ነው ያሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ።
የመሬት ቆረጣ ፣ የመሠረት ሙሌት፣ የአስባልት ፕላንት ማምረት ሥራ እየተሠራ እንደኾነም ተናግረዋል።
ከአካባቢው ማኅበረሰብ እና ከአስተዳደሩ ጋር ያላቸው መልካም መስተጋብር እና የወሰን ማስከበር ችግር አለመኖሩ ለሥራቸው መቀላጠፍ እያገዛቸው መኾኑንም ነው ያስገነዘቡት።
የመንገድ ፕሮጀክቱን አርቪ አሶሼት አርክቲክቶች እና አማካሪዎች ፒ.ኤል.ሲ ከኤስ.ጂ አማካሪ መሀንዲሶች ፒ.ኤል.ሲ. ጋር በመተባበር በጥምረት ይመራል።
የመንገድ ግንባታው በታቀደለትና በተያዘው ውል መሰረት በጥራት እየተከናወነ መኾኑን አማካሪው ዲቫካር ታህኩር (ኢንጅነር) ተናግረዋል።
ኮንትራክተሩ በታቀደለት ጊዜ መንገዱን ማጠናቀቅ የሚያስችል ቁመና ላይ እንደኾነም ነው አማካሪው ያስረዱት።
የመንገድ ፕሮጀክቱ የኅብረተሰቡን ድጋፍ ያገኘ በመኾኑ ያለምንም ችግር በታቀደለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ሌላው እድል ነው ተብሏል።
የሰሜን አቸፈር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አምሳሰው አቸነፍ በበኩላቸው የመንገድ ግንባታው የኅብረተሰቡን የረጅም ጊዜ ጥያቂያቄ የመለሰ ነው ብለውታል።
‟የመንገድ ግንባታው በወሰን ማስከበርና ተያያዥ ለግንባታው አጓታች ምክንያቶች በእኛ በኩል እንዳይፈጠሩ በትኩረት እየሠራን ነው” ብለዋል።
አሚኮ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት የመንገዱን መጠናቀቅ በጉጉት እየተጠባበቁ ነው። ‟መንገዱ በትራንስፖርት እጦት ምክንያት የሚደርስብንን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንግልት የሚቀርፍ በመኾኑ በባለቤትነት መንፈስ የሚጠበቅብንን ሁሉ እናደርጋለን” ነው ያሉት።
ዘጋቢ :- ጋሻው አደመ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/