
አዲስ አበባ፡ ሰኔ 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኦሮሚያ ክልል በንጹሃን ላይ ጭፍጨፋ የፈጸሙ የሽብር ቡድኖች ላይ የተቀናጀ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
መንግስት ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የህግ ማስከበር እርምጃ በመውሰደ ከፍተኛ ውጤት ማምጣት መቻሉን ጠቅሰው፤ የህግ ማስከበር እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
እርምጃ የተወሰደባቸው የሽብር ቡድኖች በየቦታው ችግር እየፈጠሩ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ሰሞኑን በወለጋ ጊንቢ የተካሄደው ጭፍጨፋ አንዱ ማሳያ መኾኑንም አመላክተዋል።
ከዚህ ባለፈም በጋምቤላ ክልል የነበረውን የሽብር ቡድኑን ሴራን በማክሸፍ ሙሉ ለሙሉ ወደ ሰላም መመለሱን አስታውቀዋል።
በኦሮሚያ፣ በአማራና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሚወሰዱ የህግ ማስከበር ስራዎች ውጤት እያመጡ መሆኑንም አስረድተዋል።
ሚኒስትሩ በመግለጫቸው በሀገራችን እየተንቀሳቀሱ ያሉ አሸባሪዎች በአንድም በሌላም መንገድ ከውጭ ጠላቶቻችን ጋር የሚሰሩ መሆናቸውን አንስተዋል።
ጠላቶቻችን ባገኙት አጋጣሚ የውስጥ ችግራችንን ለእኩይ ሴራቸው እየተጠቀሙበት ይገኛሉም ነው ያሉት ሚኒስትሩ።
የሽብር ሥራው ምንጩ ከውኃ ፓለቲካ እና ከቀጣናዊ ፓለቲካ የሚመነጭ እና በተላላኪ የሚፈፀም መኾኑን ኅብረተሰቡ ሊረዳው እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት፡፡ ሴራውን በመረዳት አንዴ ብሔር ሌላ ጊዜ ሃይማኖት ሊያደርጉት የሚፈልጉትን ትቶ የትም ይሁን የት የሞተው ንፁህ ሰው መኾኑን መረዳት እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡
አሸባሪው ኀይል፤ መንግሥትን ከሕዝብ የመነጠል እሳቤ ይዞ መንቀሳቀሱን የተናገሩት ዶክተር ለገሰ ለዚህ ደግሞ ሕዝቡ አንድነትን አጥብቆ በመያዝ እኩይ ተግባርን እንዲከላከል አሳስበዋል፡፡
ዶክተር ለገሰ በመግለጫቸው መንግሥት ለትግራይ ሕዝብ እርዳታ በየብስ እና በአውሮፕላን እያደረሰ ቢኾንም አሸባሪው የትህነግ ቡድን ሕዝቡን ለሌላ ጥፋት ለማሰማራት እየተንቀሳቀሳ መኾኑንም መንግስት ደርሶበታል ብለዋል፡፡ በመንግሥት በኩል ግን የሰላም አማራጮች ላይ ለመወያየት ዝግጁ እና ፍቃደኛ እንደኾነም አስረድተዋል፡፡
ቀጣይ ኢትዮጵያ ሶስተኛውን የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የውኃ ሙሌት የምታከናውን እና ተጨማሪ ኀይል የምታመነጭበት ጊዜ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ኅብረተሰቡ አንድነቱን አጣናክሮ የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ የአረንጓዴ አሻራውን በማስቀመጥ በእርሻ ሥራው ምርታማነት ላይ ሊያተኩር ይገባል ነው ያሉት፡፡
ዘጋቢ፦ አብነት እስከዚያ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/