
ባሕር ዳር: ሰኔ 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኀላፊ ግዛቸው ሙሉነህ በወቅታዊ ጉዳዮች መግለጫ እየሰጡ ነው።
በመግለጫቸውም ውስጣዊ አንድነትን ለማጠናከር እና የውጭ ጠላትን ለመመከት የሕግ ማስከበር ሥራ መጀመሩን ገልጸዋል። የክልሉ የፀጥታ ምክር ቤት የሕግ ማስከበሩን ሂደትና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጉን አስታውቀዋል።
በሕዝብ ጥያቄ መሠረት የሕግ ማስከበር መጀመሩን አንስተዋል። የሕግ ማስከበር ሥራው ውጤት የታየበት መኾኑን የፀጥታ ምክር ቤቱ መገምገሙንም ገልጸዋል። ጉድለቶችንም መመልከቱን ነው የተናገሩት።
ክልሉ ወደ ሰላም መምጣቱንም አንስተዋል። በርካታ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም ጠቁመዋል። ከፀጥታ ኀይል የከዳ ኀይልም መያዙን ነው የተናገሩት።
በሕግ ማስከበሩ ሥራ የፀጥታ ተቋማት ራሳቸውን ያደራጁበት መኾኑንም ገልጸዋል። ለክልሉ ስጋት ለኾኑ ጠላቶች ዝግጁ መኾኑን ያሳየበት መኾኑን አመላክተዋል። የሕግ ማስከበር ሥራው ለሽብር ተልዕኮ የሚንቀሳቀሱ አካላትን መልክ ያስያዘ መኾኑንም አስታውቀዋል። ለጠላት ሲላላኩ የነበሩ የሽብር አካላት በቁጥጥር ሥር ውለዋልም ነው ያሉት።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/