
ባሕር ዳር: ሰኔ 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገራዊ ምክክር ለኢትዮጵያ የጋራ ጉባኤ በባሕር ዳር ተጀምሯል። የደኅንነት ጥናት ተቋም እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በጋራ ያዘጋጁት ሀገራዊ ምክክር ለኢትዮጵያ፣ አስፈላጊነት፣ ሂደት፣ የባለ ድርሻ አካላት ሚና እና የቢኾን ትንተናዎች የጋራ ጉባኤ ተጀምሯል።
በጋራ ጉባኤው በደኅንነት ጥናት ተቋም እና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባለሙያዎች እና ተመራማሪዎች የተዘጋጁ ጥናታዊ ጹሑፎች እና የቢኾን ትንተናዎች ይቀርባሉ። በተመራማሪዎቹ የሚቀርቡት ጉዳዮች የሀገራዊ ምክክር አስፈላጊነት፣ በታሪካዊ እና ንጽጽር እይታ፣ ለተሳካ ሀገራዊ ምክክር አስፈላጊ ሁኔታዎች፣ ለሀገራዊ ምክክር የባለድርሻ አካላት ሚና፣ ኢትዮጵያ ከስኬታማ አሊያም ከተሰናከለ ሀገራዊ ምክክር በኋላ፤ ምጥን የቢኾን ትንተናዎች በሚሉ ርዕሶች ይቀርባሉ።
በምክክር ጉባኤው ላይ የተገኙት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፍሬው ተገኘ (ዶክተር) ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔሮች፣ ቋንቋዎች፣ ባሕል እና እሴት ባለቤት ናት ብለዋል። እነዚህ ጸጋዎች በሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ላይ በጎ ተጽዕኖ ነበራቸው ያሉት ዶክተር ፍሬው ከሌሎች የአፍረካ ሀገራት በተለየ ነጻነት እንዲኖራት አድርገዋል ብለዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የልሂቃን ተቃርኖ እና የፓለቲካ መካረር እየተስተዋለ መምጣቱን ያወሱት ፕሬዝዳንቱ በውይይት እና በምክክር ልዩነቶችን ማጥበብ እና መካረሮችን መግታት ያስፈልጋል ነው ያሉት። “የጋራ ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግሥት ማቆም የትውልዱ ኅላፊነት ነው” ያሉት ዶክተር ፍሬው ከዛሬ ላይ ብቻ ተንጠልጥለን እና ችግሩን አቅልለን ካየነው መፍትሄ ላይ መድረስ ይከብዳል ብለዋል። ከችግሩ መነሻ ምክንያት ላይ ትኩረት ማድረግም የምክክር ጉባኤው ዓላማ መኾኑንም አንስተዋል።
በምክክር ጉባኤው የፌዴራል እና የክልል የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኅላፊዎች፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ተማሪዎች፣ የደኅንነት ጥናት ተቋም ተመራማሪዎች ተሳታፊዎች ናቸው።
ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
