በባሕርዳር ከተማ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም የተንቀሳቀሱ አካላት በቁጥጥር ስር ዋሉ።

379

ባሕር ዳር: ሰኔ 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕርዳር ከተማ ውስጥ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም የተንቀሳቀሱ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ገልጿል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር መሰረት ደባልቄ በሰጡት መግለጫ “በሀገሪቱና በክልሉ ሕግ ለማስከበር እየተንቀሳቀስን እንገኛለን” ብለዋል፡፡ በተለይም በአማራ ክልል የተደራጁ ሕገወጦችን ወደ ሕግ ለማቅረብ ሲሠራ ቆይቷል ነው ያሉት።
የኀብረተሰቡን የሰላም ጥያቄ በማዳመጥ በተወሰደው ሕግ የማስከበር ርምጃም አብዛኞች ጥፋተኞች ወደ ሕግ ቀርበው እፎይታ ተገኝቷል ብለዋል።
በዚኽ ሕግ የማስከበር ሂደት ሕዝቡ ያገኘውን እፎይታ እየገለጸ ባለበት ወቅት ሰኔ 20/2014 ዓ.ም ምሽት ኅብረተሰቡን ለማሸበር ያለመ ወንጀል መፈፀም የፈለጉ ቀሪ ኀይሎች በባሕርዳር ከተማ በአራት ቦታዎች ላይ ቦንብ እንዳፈነዱ ገልጸዋል።
ፓሊስ ከሕዝብ ጋር በመቀናጀት ባደረገው ክትትልም ወዲያውኑ ስድስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር አውሏል ነው ያሉት።
የተጠርጣሪዎች ቤት በሚፈተሽበት ወቅትም 2 ቦንብ፣ 3 ብሬን መሳሪያ እና 3ሺህ 700 ጥይት፣ አንድ ስናይፐርና አምስት መቶ ጥይት እንዲኹም በቀጣይም ተመሳሳይ የሽብር ወንጀል ለመፈፀም የያዙትን እቅድና መመሪያ ፓሊስ መያዙን ኮማንደር መሰረት ጠቁመዋል።
በዚሁ ምሽት ከዚሁ ሽብር ጋር ግንኙነት ያላቸው 14 ተባባሪ አካላት በቁጥጥር ስር ውለው የክልልና የፌዴራል የፀጥታ አካላት ምርመራ እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።
ፓሊስ የሚደርስበትን የምርመራ ውጤት ወደፊት ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደረግም ተናግረዋል።
ሕዝቡ መሰል የሽብር ድርጊቶችን ለመከላከል አካባቢውን ነቅቶ መጠበቅ እንዳለበትም ኮማንደር መሰረት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ:–አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ግጭት አድራቂ የሰላምና እርቅ መድረኮች የፍቅር በር መክፈት አለባቸው” የአማራ ክልል እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሰላምና የልማት ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት
Next articleየስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ወደ ቀደመ የብዝሃ ሕይዎት ገጽታው ተመልሷል፡፡